የሴቶች ፣ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ የሴቶች ፣ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ

ስለ ቢሮው

የተቋቋመበት ደንብ፡-

 • በአዲሰ አበባ ከተማ አሰተዳደር የሴቶች.ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 361/2003

የተቋቋመበት ዘመን፡-

 • ቀደም ሲል በማህበራዊና ሲቪል ጉዳዪች ቢሮ ሰር የሴቶች ጉዳይ ጽ/ቤት በሚል መጠሪያ የነበረ ሲሆን  በአዋጅ 2000 ዓ.ም ራሱን ችሎ ወደ ቢሮ ደረጃ አደገ በ2001 ዓ.ም ከህጻናት ጋር በመቀላቀል የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ እየተባለ ሲጠራ ቆይቶ በ2003 ዓ.ም ደግሞ ወጣቶችና ጉዳይ ቢሮ በመባል ተቋቁሟል፡፡

ራዕይ፡-

 • በ2012ዓ.ም በአዲሰ አበባ ከተማ የስርአተ ጻታ እኩልነት የሰፈነበት የህጻናት መብትና ደህንነት የተከበረበት ህብረተሰብና ስብዕናው የተሟላ በሀገር ግንባታ ሂደት ተሳታፊና ተጠቃሚ የሆነ ወጣት መፍጠር፡፡

ተልዕኮ

 • በአዲሰ አበባ ከተማ በህብረተሰቡ ዘንድ ግንዛቤ በመፍጠር፣ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ህዝባዊ መሰረት ያላቸው አደረጃጀቶችን በማጠናከር የንቅናቄና ተሳትፎ ፕሮግራሞችን በመዘርጋት ወጣት ማዕከላትን በማስፋፋትና በማበልፀግ ማህበረሰብ አቀፍየህጻናትን ድጋፍና ክብካቤ አገልግሎት በመስጠትና ህፃናትን መብትና ደህንነት በማስከበር እንዲሁም ሁሉንም ሴክተር መ/ቤቶች የሴቶችና የወጣቶች ጉዳይ በእቀዶቻቸው ውስጥ አካተው እዲሰሩ በማድረግ ከተማዋን ሴቶችና ወጣቶች በሁሉም መስክ እኩል ተሳታፊ ተጠቃሚና ውሳኔ ሰጪ እዲሆኑ ማድረግ፡፡

እሴቶች

 • ተጠያቂነት
 • ግልፅነት
 • ለለውጥ ዝግጁነት 
 • የላቀ አገልግሎት መስጠት 
 • በእውቀትና  በእምነት መመራት/መስራት
 • ለህፃናትና ሴቶች መብት መከበር መትጋት 
 • የስርዓተ ጾታ እኩልነትን ማረጋገጥ
 • ወጣቱን ግንባር ቀደም የልማት ኃይል አድረጎ ማንቀሳቀስ

የመሥሪ ቤቱ ሰራተኛ ብዛት ፡- ወንድ-121፣ሴት፣160፣ ድምር 28