ምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ ምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ

H.E. Dr. Tabor G.Medihin - Speaker of the Council

በአገራችን እየተፋጠነ ያለውን ሁለንተናዊ ዕድገት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና ለህዝቡ ተጠቃሚነት መረጋገጥ የምክር ቤቶች ሚና በማንም የማይተካ  ነው፡፡ በመሆኑም ምክር ቤቶች ሕግ ከማውጣት ባሻገር አስፈፃሚ አካላትን የመከታተልና የመቆጣጠር ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል፡፡ ክትትልና ቁጥጥር የሚያደርጉበት መሠረታዊ ምክንያትም በሕገ መንግስቱና በቻርተሩ የተሰጣቸው ሥልጣን  በመሆኑና ህዝቡም ጥቅሜን ያስጠብቁልኛል ብሎ በማመን በቀጥተኛ ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ የተወከሉ በመሆናቸው ነው፡፡ ስለዚህ የመንግስት  ፓሊሲዎችና ስትራቴጂ እንዲሁም የከተማው ዕቅዶች በአግባቡ እንዲተገበሩ ፤ የሚታዩ የአፈፃፀም እጥረቶችም ስር ሳይሰዱ እንዲታረሙ የማድረግ ሀላፊነት ተጥሎባቸዋል፡፡  በክትትልና ቁጥጥር ስራው አማካኝነት መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን፣ የዚህ መርሆ የሆነው የግልጽነትና የተጠያቂነት የአሰራር ሥርዓት እንዲጎለብት የላቀ ትግል ማድረግም  ይጠበቅባቸዋል፡፡

ከዚህ አንጻርም በዘንድሮው ዓመት በተለይ በጥልቅ ተሀድሶ ማግሰት ምክር ቤታችን ከመቼውም ጊዜ በላይ የህዝብ ጥቅምን ለማስከበር ጥረት አድርጓል፡፡ ይኸውም ከተማ ምክር ቤቱን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ የህዝብ ምክር ቤቶች ወጥነት ያለውና የተጠናከረ ተቋማዊ አደረጃጀትና አሰራር ስርዓት ፈጥረው እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ መጠነ ሰፊ ተግባራት ተከናውኗል፡፡ ከነዚህም መካከል ምክር ቤቱ በዝግጅት ምእራፍ የተጣለበትን ህዝባዊ አደራ ለመወጣት የሚያስችል ዕቅድ አዘጋጅቶ ያለፈውን ዓመት ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት በመገምገም በየደረጃው የሚገኙትን የም/ቤት አባላትና የዘርፍ ኮሚቴ አመራሮችን መልሶ የማደራጀት ስራ ሰርቷል፡፡ የምክርቤታችንን የቋሚ ኮሚቴ አወቃቀር በማሻሻል አዳዲስ ዘርፎችን በማካተት የቋሚ ኮሚቴ ቁጥር እንዲጨምር ተደርጓል፡፡ይህም ለቁጥጥርና ክትትል ተግባሩ እንዲጎለብት ለማድረግ ነው፡፡

በሌላ በኩል ም/ቤቱ ከከተማ እስከ ወረዳ ያሉ የምክር ቤት አባላት 

በየአደረጃጀታቸው በጥልቅ ተሃድሶው እንዲያልፉ የተደረገ ቢሆንም ከምክርቤት አባላት ሚና ጋር በማያያዝ

Honorable Tesfaye Terfesa Vice Speaker

 ስልጠና እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡  በተጨማሪም ምክር ቤቶች ህዝብ የጣለባቸውን ከፍተኛ ሃላፊነት በተሟላ እውቀትና ክህሎት  እንዲፈጽሙ ከፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በምክር ቤቶች ሚናና አሰራር እንዲሁም በክትትልና ቁጥጥር አፈጻጸም ላይ ሰፊ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

 
ምክር ቤቱ ህግ ከማውጣት ባሻገር መርህን መሰረት ያደረገ የክትትልና የቁጥጥር ድጋፍ ተግባራትን አከናውኗል፡፡ የ

ግልጽነትና ተጠያቂነት የአሰራር ስርዓትን መሰረት በማድረግ በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ትርጉም ባለው ሁኔታ በመቅረፍ ለተያያዝነው የእድገትና የመልካም አስተዳደር መስፈን እንቅፋት የሚሆኑ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትን ተግባራትን በማዳከም ስር ነቀል ልማታዊ አስተሳሰብ የበላይነት እንዲኖረው ለማድረግ የህዝብ አስተያየትና ጥቆማ እንደ ግብዓት በመጠቀም በአስፈ

ጻሚ አካላት ዕቅድና አፈጻጸም ዙሪያ በተደራጀ ሁኔታ ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም ድጋፍ ከማድረግ አንጻር አበረታች ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡
 

ቋሚ ኮሚቴዎቻችን የሚከታተሏቸውን አስፈጻሚ አካላት ዕቅድ አፈጻጸማቸውን በማዳመጥና እያንዳንዱ ሴክተር መስሪያ ቤት አፈጻጸም ከተቋቋመበት ዓላማና ተልእኮ አንጻር የተቃኘ ስለመሆኑ በመገምገም እንዲሁም በአፈጻጸሙ የተገለጹ ስራዎችን መስክ ወርደው ያሉበትን ደረጃ በመመልከት ግብረመልስ ተሰጥቷል፡፡የሪፖርቶችን ተአማኒነት ለማረጋገጥ ሪፖርትን መሰረት ያደረገ የመስክ ምልከታ  በማካሄድ ከሀላፊዎች ጋር ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በመጨረሻም ም/ቤቶች ከመረጣቸው  ህዝብ ጋር በቅርበት በመገናኘት የህዝብ አቤቱታዎችንና ቅሬታዎችን ወቅታዊና ተገቢ ምላሽ እንዲያገኙ በማድረግ የህዝብ መድረኮችን በመፍጠር የህዝቡን ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ በማሳደግ ረገድም ከፍተኛ ሃላፊነት ለመወጣት ጥረት ተደርጓል፡፡ በዚህ ላይ መልካም ጅምሮች ቢኖሩም ከህዝባችን ፍላጎት አንጻር ብዙ መስራትን ይጠይቃል፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃም የመንግስትን የልማት ግቦች ለማሳካትና በከተማችንም የተጀመሩ የልማት፣ የመልካም አስታዳደርና ማህበራዊ አግልግሎቶች እንዲጠናከሩ ለማድረግ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባርን በመድፈቅ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አንጻርም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ህብረተሰቡም ከመረጠው ወኪሉ ጋር እጅ ለእጅ በመያያዝ ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታውና አጠቃላይ አገራችን ዕድገት የሚፈልገውን ተሳትፎ በማሳደግ ተጠቃሚነቱን ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡