ታሪካዊ መስህቦች ታሪካዊ መስህቦች

ታሪካዊ አብያተ ክርስትያናት   
 

እንጦጦ ደ/ሀይል ቅዱስ ራጉኤል /ደብረ ኤልያስ ቤተክርስቲያን  
Entoto Raguel-Eliasአጼ ዳዊት ያርፉበት በነበረው ቦታ ጥር 30 ቀን 1872 ዐ.ም በአጼ ሚኒሊክ ተሰራ፡፡ የቤተክርስቲያንዋ ህንጻ ከድንጋይ፣ ከኖራ፣ ከአሸዋ፣  ከመናገሸ በመጣ ጽድ የተሰራ ሲሆን   እንደሲሚንቶ የተጠቀሙት የእንቁላል አስከዋልና የበሬ ቆዳ በመቀቀል ነበር፡፡ ቤተክርስቲያኗ በእንጦጦ ተራራማና ዳገታማ አከባቢ ትገኛለች፡፡

እንጦጦ ሀመረኖህ ኪዳነ-ምህረት ገዳም  
እንጦጦ ሀመረኖህ ኪዳነ-ምህረት ገዳም ገዳሟ የተቆረቆረችው በ484 አ.ም ሲሆን በ500አ.ም ደግሞ አባ ሊባኖስ በተባሉ ጻዲቅ መነኩሴ ገዳም ሆና ተቋቋመች፡፡ በአጼ ሚኒሊክ ዘመን እቴጌ ጣይቱ ወደ ገዳሟ በመምጣት እድሳት እንዲደረግላት አዘዙ፡፡ በ20 ከ/ዘመን ዘውዲቱ ይህቺን ገዳም ሀመረ ኖህ ብለው ሰይመው የህንጻው ግንባታ አስጀምረው በአጼ ኀ/ስላሴ ባለቤት እቴጌ መነን ትዛዝ ግንባታው አልቋል፡፡ ህንጻው የመርከብና የመስቀል ቅርጽ የያዘ ሲሆን ከጥርብ ድንጋይ ከመናገሻ በመጣ ጽድ ፤ከቆርቆሮ እና ከመስታወት የተሰራ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ በ ጉ/ክ/ከ ወረዳ1 ትገኛለች፡፡  

 

 

ምስካየ ህዙናን መድሀኔአለም ገዳም   
ምስካየ ህዙናን መድሀኔአለም ገዳም ገዳሙ ለተፈሪ መኮንን ት/ቤት አዳሪ ተማሪዎች መጸለያ ፣መንፈሳዊ ት/ቤት መማሪያና የአምልኮ ቦታ እንዲሆን በ አጼ ኀ/ስላሴ ተእዛዝ ተሰራ፡፡ ታቦቱ በእስራኤል ጼር ሱልጣን ይባል በነበረ ቦታ የነበረ ሲሆን አፄ ኀ/ስላሴ በአምስት አመቱ የጣሊያን ወረራ በስደት በቆዩበት እንግሊዝ ሀገር አስመጥተዉ ከነፃነት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ይዘዉት ሊመጡ ችለዋል፡፡ የቤተክርስቲያኑ ህንጻ ግንባታ እስኪጠናቀቅም ታቦቱ በየካቲት12 ሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ እንዲቆይ ከተደረገ በኋላ ሚያዛ27 ቀን 1942 አ.ም የቤተክርስቲያኑ ህንጻ ሲጠናቀቅ  ታቦቱ ወደገዳሙ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሶስት የአብነት ት/ት ማለትም የመጽሀፍት ትርጓሜ ፣የቅኔና የቅዳሴ ት/ት ይሰጥበታል፡፡ በውስጡም አጼ ኀ/ስላሴና እቴጌ ጣይቱ ይጸልዩባቸው የነበሩ ወንበሮች ፣ልዩልዩ ምንጣፎች የብራና መጽሀፍትና መንፈሳዊ ስእሎች ይገኛሉ፡፡ ምስካየ ህዙናን በግእዝ የምስኪኖች መጠጊያ ማለት ነው፡፡

 

ጸርሀ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል ቤ/ክርስቲያን  
ምስካየ ህዙናን መድሀኔአለም ገዳም በፊት አውራሪ ሀብተጊዮርጊስ አማካኝነት በ1907 ተገነባ፡፡ቤተ-ክርስቲያኑ ያረፈበት ቦታ አጼ ሚኒሊክ ለእስፖርት ትእይንት ወደ ጉለሌሲመጡ ያርፉበት የነበረ ቦታ እንደነበር ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያኑ በጉ/ክ/ከወረዳ 9 ሸጎሌ አካባቢ

ቀጨኔ ደብረ-ሰላም መድኀኔዓለም  
ቀጨኔ ደብረ-ሰላም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያኑ አሁን የሚገኝበት ቦታ  የተመረጠዉ በልጅ እያሱ ሲሆን ይኸዉም፡-ጦራቸውን ሶስት ጊዜ ወርረው በመጀመርያ ያረፈበትን ቤተክርስቲያኑ አንዲሰራ ሲያደርጉ ሁለተኛ ጊዜ ያረፈበትን ደግሞ  የደውል ቤቱ እንዲሰራበት አደረጉ፡፡ ግንባታዉንም ልጅ እያሱ አስጀምረውት ንግስት ዘውዲቱ አስጨርሰውታል፡፡ በግቢዉ ውስጥ በቅርብ ጊዜ የተሰራዉ ሙዚየም በርካታ ተንቀሳቃሽ ቅርሶች ያካትታል፡፡ ይኸዉም የልጅ እያሱ አልጋ ፣አገልግል፣ለምድ፣የንግስት ዘውዲቱ እና የእያሱ ዘውዶች ፣መስቀል፤ድጓ ወ.ዘ.ተ ናቸዉ፡፡ ቀጨኔ ደብረ-ሰልም መድኀኔአለም በጉ/ክ/ከ ወረዳ4  ቀጨኔ አካባቢ ይገኛል፡፡

 

መንበረ ንግስት ቁስቋም ማሪያም ቤ/ክርስቲያን  
መንበረ ንግስት ቁስቋም ማሪያም ቤ/ክርስቲያን በ1919 ዓ.ም ቤተ ክርስቲያንዋን ከጥቁር ደንጋይ  ከጽድ እንጨት ከቆርቆሮ እና ከኖራ ያሰሩት አፄ ኃ/ስላሴ ናቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያንዋ ያረፈችበት ቦታ አጼ ሚኒሊክ ከ እንጦጦ ወደ ፍል ውሀ ሲመላለሱ  ድንኳዋን ተክለው ያርፉበት የነበረው ቦታ ሲሆን አንድ ቀን በድንኳናቸው ተኝተው እያሉ በህልማቸው አንድ ሴት ይህን ቦታ ቤት ልስራበት ልቀቅልኝ እንዳለቻቸው እሳቸውም  እመቤቴ ማርያም ናት በሚል ቦታውን ለቤ/ክርስቲያን ማሰሪያነት ፈቅደው ግነባታውን  እንዳስጀመሩት ይነገራል፡፡   ግንባታውንም   አጼ ኀ/ስላሴ አጨርሰውታል፡፡

መንበረ ፀሀይ እንጦጦ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን
ቀጨኔ ደብረ-ሰላም መድኀኔዓለም በ1870 አ.ም  በአጼ ሚኒሊክና በእቴጌ ጣይቱ ተሰርቶ በ1913 በንግስት ዘውዲቱ በድጋሚ እድሳት ተደረገለት፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ የታነፀችበት ቦታ አዲስ አበባ ከመቆርቆሯ በፊት በ12ኛዉእና በ13ኛዉ ክ/ዘመን መጀመሪያ ዎቹ ዋና ከተማ እና  የተለያዩ ነገስታት ማረፊያ እንደነበረ ይነገራል በተጨማሪም፡-አፄ ምኒሊክ በ መጀመሪያ ጊዜ ሰራዊታቸውን ይዘው የሰፈሩትም በዚሁ አካባቢ  ነበር፡፡ ቤተክርስቲያንዋ ባለ ሶስት ክፍል ስትሆን ቅድስት፡ መቅደስና ፤ቅኔ ማህሌት ናቸው፡፡ ባለ 8መአዘን የሆነው የቤተክርስቲያንዋ ህንጻ ከጥርብ ድንጋይ፡ ከዝግባ እንጨት  የተሰራ ነው ፡፡የእየሱስ ግማደ መስቀል ከእየሩሳሌም በአጼ ዳዊት ዘመነ መንግስት ወደ  ሀገራችን ሲመጣ በዚችው ቤ/ክርስቲን ለ3ቀን አርፎ እንደነበር  ከዚያም ወደ ደ/ብርሃን መሄዱ ይነገራል፡፡ ቤተ-ክርስቲያኗ በእንጦጦ ጫፍ ከአጼ ምንሊክ ቤተ መንግስት አጠገብ ትገኛለች::

 

መንበረ ልኡል ቅዱስ ማርቆስ  
መንበረ ልኡል ቅዱስ ማርቆስ በቀደማዊ ኃ/ስላሴ ትእዛዝ በደጃዝማች ወንድራድ አመካኝነት ተሰራ፡፡ 6 ኪሎ ዩኒቨርስቲ ጎን ይገኛል፡፡

 

 

 

ጅፋሬ ድልድይ  
 በ1962ዓ.ም እንደተሰራ ይነገራል፡፡ አከባቢው በልማት ኃላ ቀር በነበረበት ግዜ በዘመናዊ መልኩ የተሰራ ሲሆን በአፄ፡፡ ከድንጋይ ፣ከሲሚንቶና ከሌሎች ቁሳቁሶች እንደተሰራ ያሳያል፡፡ ከአዲሱ መንገድ ወደ ቀጨኔ መድሀኔ አለም በሚወስደው መንገድ ጅፋሬ ሰፈር ፊት ለፊት ይገኛል፡፡           

እንጠጦ ታሪካዊ ቦታ   
እንጠጦ ታሪካዊ ቦታ እንጠጦ ከአዲስ አበባ በስተ ሰሜን አከባቢ የሚገኝ ተራራማ፣ዳገታማናጥቅጥቅ ባለ ደን የተሸፈነ ማራኪ ቦታ ነው፡፡አከባቢው የአጼ ዳዊት  እና የአጼ ምኒሊክ ጨንምሮ የበርካታ ነገስታት መኖርያ እንደነበር የተለያዩ የታሪክ አሻራዎች ይጠቁማሉ፡፡ባከባቢዉ ከሚገኙ ቅርሶች መካከል ፣ የአጼ ዳዊት፣ የአጼምኒልክ ቤተ መንግስት እንደነበረ የሚያመላክት የቤተ-መንግስት ፍርስራሽ፣   አብያተ ክርስትያናት፣ታሪካዊ ዋሻዎች፣ እና ደኖች ተጠቃሽ ናቸው፡፡   አጼ ምኒልክ በ1870ዓ.ም አከባቢ 50 ሺህ ያህል ሰራዊታቸውን ይዘው በእንጠጦ አካባቢ ሰፍረው እንደነበር ታሪክ ያስረዳል፡፡ አፄ ምንሊክ በወቅቱ ለነበረው የማገዶ እንጨት እጥረት መፍትሄ ይሆን ዘንድ ባህር ዛፍ ከአውስትራልያ በማስመጣት በዙሪያው አስተክለዋል፡ በወቅቱ ከተተከሉት ዛፎች መካከልም አንዱ በቤተ መንገሰታቸዉ ግቢ ዉስጥ ይገኛል፡፡እንጠጦ በርካታ የሀገር ዉስጥ እና የዉጭ ቱሪስቶች ከሚጎበኟቸዉ ስፍራዎች መካከል አንዱ ሲሆን  ለዚህም ምክንያቱ ተፈጥሯዊ ዉበቱ እና በተለያዩ ዘመናት ባካባቢው የተፈጸሙ ታሪካዊ ክስተቶች  ናቸው፡፡

 

ገጾች: 1  2  3