ቅርሶችና ሐውልቶች ቅርሶችና ሐውልቶች


ዋሻዎች
የአጼ ዳዊት ዋሻዎች
የአጼ ዳዊት ዋሻዎችከ1375- 1380 ዐ.ም የ አጼዘረያቆብ አባት በነበሩት በ አጼዳዊት ተሰራ፡፡ ዋሻው በኮከብ ቅርጽ የተሰሩ 3 ክፍሎች ያሉት ከአንድ ድንጋይ ተፈልፍሎ የተሰራ ነው፡፡ በአጼ ዳዊት ዘመነ መንግስት የንጉሱ ውድ እቃዎች ማስቀመጫነት ያገለግል የነበረ ሲሆን   በ15 ኛው ክ/ ዘመን  የግራኝ አህመድ ወታደሮች እንደ ምሽግ ተጠቅመዉበታል፡፡ በአጼ ምኒልክ ዘመን የቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስትያን ከመሰራቱ በፊት የታቦቱ ማኖርያ ሆኖ አገልግሏል፡፡ በእንጦጦ ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስትያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛል፡፡

 

 

 

 

 

 

አለሙ አዋሽ ዋሻ  
በ1927ዓ.ም አቶ አለሙ የተባሉ የአከባቢው ነዋሪ ከጣልያን ወረራ መሸሸግያነት ያሰሩት ጥልቀትያለው ዋሻ ነዉ፡፡ታሪካዊ ዋሻ በመሆኑ ለቱሪስት መስህብነት ጠቃሚ ነው፡፡ ከእንጠጦ ቅ/ራጉኤል ቤተ ክርስትያን በስተ ሰሜን ምእራብ በኩል መንገዱን ተሻግሮ ከምፅላል ግርማ ዋሻ ጎን ይገኛል፡፡

ምፅላል ግርማ ዋሻ ምፅላል ግርማ ዋሻ  
በ1927ዓ.ም ባከባቢው ታዋቂ በነበሩ ርእሰ ደብር ምፅላል ግርማ እና በወንድሞቻቸው ተሰራ፡፡ ከጣልያን ወረራ መሸሸጊያ እንዲሆን ታስቦ የተሰራ፡፡ ከእንጠጦ ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስትያን በስተምእራብ በኩል የንጉስውሃ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ይገኛል፡፡

 

 

ገ/ሚካኤል ወ/ፃድቅ ዋሻ  
በ1928ዓ.ም አቶ ገ/ሚካኤል በተባሉ ነዋሪ የተሠራ ታሪካዊ ዋሻ ነው፡፡ ከጣልያን ወረራ መሸሸጊያ እንዲሆን ታስቦ የተሰራ፡፡ ከእንጠጦ ቤተ ክርስትያን በስተ ሰሜን ምእራብ ከምፅላል ግርማ እና ከአለሙ አዋሽ ዋሻዎች አጠገብ ይገኛል፡፡

መልአከ ኃይል ተድላ ወልደ ፃድቅ ዋሻ   
መልአከ ኃይል ተድላ ወልደ ፃድቅ ዋሻ በ1927ዓ.ም የቅዱሰ ራጉኤል ቤተ ክርስትያን አስተዳዳሪ በነበሩት በመልአከ ኃይል ተድላ ተሠራ፡፡ ዋሻው በሰው እጅ ተፈልፍሎ የተሰራና በወቅቱ የነበረው የኢትዮጵያውያንን ጥበብ የሚያመላክት ነው፡፡ ከጣልያን ወረራ መሸሸጊያ እንዲሆን ታስቦ የተሰራ፡፡ ከእንጠጦ ቅ/ራጉኤል በስተ ሰሜን ምእራብ አቅጣጫ በግምት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል፡፡

 

ገጾች: 1  2  3