ቅርሶችና ሐውልቶች ቅርሶችና ሐውልቶች

የካርል ማርክስ ሐዉልት
የካርል ማርክስ ሐዉልትበደርግ መንግስት 10ኛው የአብዮት በአል በማስመልከት ከጀርመን ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ የተሰጠ፣በሐዉልቱ ጀርባ የሁሉም አገር ሰራተኞች ተባበሩ የሚል ፅሁፍ አለው፡፡ ርዝመቱ 3ሜ ከ 65ሳ.ሜ፣ ወርዱ 1.30ሜ፣ ዉፍረቱደግሞ 4ሜ ከ48ሳ.ሜ ነው፡፡ ሐዉልቱ ከእምነበረድ የተሰራ ሲሆን በስድስት ኪሎ ዩኒቨርስቲ ዋናው በር ፊት ለፊት ድባብ መናፈሻ ዉስጥ ይገኛል፡፡

 

 

 

የኢትዮጵያን የኮርያ ዘማቾች መታሰብያ ሐዉልት
የኢትዮጵያን የኮርያ ዘማቾች መታሰብያ ሐዉልትየካቲት 19 ቀን 1998ዓ.ም በ አ/አበባ ከተማ መስተዳድር በኮሪያ መንግስት ትብብር ተሠራ፡፡ ኢትዮጵያ ከ60 ዓመታት በፊት በተባበሩት መንግስታት ጠያቂነት አለም አቀፍ ደህንነት ለማስጠበቅ የተወጣችውን ግዴታ ያሳያል፡፡ በወቅቱ የተሰዉ 122 የሚሆኑ የጦሩ አባላት አስክሬን የመጣባቸው 122 ሳጥኖች በግቢዉ ዉስጥ በተሰራዉ ሙዚየም ዉስጥ ይገኛሉ፡፡ ሐዉልቱ አፍንጮ በር ፓርክ ዉስጥ ይገኛሉ፡፡

የቀዳማዊ ኃ/ስላሴ የመታሰብያ ሐዉልት
የቀዳማዊ ኃ/ስላሴ የመታሰብያ ሐዉልትበ1917ዓ.ም በአልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን እንደተሰራ ይነገራል፡፡ ከአንድ ድንጋይ ተፈልፍሎ በመሰራቱ ና ከታሪካዊነቱ አንጻር ለቱሪስት መስህብነት ያገለግላል፡፡ ሐዉልቱ እንጠጦ ቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ዉስጥ ይገኛል፡፡

 

 

 

የዶ/ር እንግዳ ዮሃንስ መታሰብያ ሐዉልት
የዶ/ር እንግዳ ዮሃንስ መታሰብያ ሐዉልትየካቲት 17 ቀን 1941ዓ.ም በቀ/ኃ/ሥላሴ ትእዛዝ ተሠራ፡፡ ዶ/ር እንግዳ በእንስሳት ዙርያ ጥናት ና ምርምር ያደርጉ ስለነበር በሐውልቱ ዙሪያ የተለያዩ የቤት እንስሳት እና የግለሰቡ ፎቶግራፎች እንዲሁም ግለ ታሪክ ይገኛል፡፡ ሐዉልቱ በእንጠጦ ቴክኒክና ሙያ ግቢ ዉስጥ ይገኛል፡፡

 

 

 

የራስ መኮንን መታሰቢያ ሐዉልት   
የዶ/ር እንግዳ ዮሃንስ መታሰብያ ሐዉልትበ1955ዓ.ም አከባቢ ቀ/ኃ/ሥላሴ ለአባታቸው እንዳሰሩት ይነገራል፡፡ ሀውልቱ በ6 ኪሎ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጲያ ጥናት እና ምርምር ተቋም ውስጥ ይገኛል፡፡

ገጾች: 1  2  3