ቅርሶችና ሐውልቶች ቅርሶችና ሐውልቶች

ግብይት
ገብያ የተለያዩ እቃዎች የሚለዋውጥበት እና እንዲሁም እንደ ዋና ማሕበራዊ ግንኑነቶችን ከሚፈጥሩ ነገሮች መሃከል አንዱ ሆኖ የሚያገልግል ቦታ ነው፡፡ ገበያ እንደ ኢትዮጵያ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰብ ያሉዋት ሃገራት ከፍተኛ ጠቀሜታ መኖሩንና የሃገሪትዋ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ባህልና ልምድ አጉልቶ የሚያሳይ ነው፡፡

መርካቶ
መርካቶ በአፍሪካ ውስጥ አሉ ከሚባሉ ታላላቅ ገበያዎች መሃከል አንዱ ነው፡፡ በማንኛውም ቀን በመቶ ሺዎች ከሚቆተሩ ሻጮችና ተጠቃሚዎች መሃከል ግብይት ይፈፀማል፡፡ መርካቶ በተለያዩ እቃዎች በመሸጥ ሂወታቸውን ለሚመሩ የሃገሪትዎ ተለያዩ ብሄር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የምታገናኝ ስፍራ ናት፡፡ መርካቶ ባህላዊና ዘመናዊ የሆኑት የግብይት ስርዓቶች አንድ ላይ አጣምራ የምትሄድ ቦታ እና የቱሪስት ምንጭ ናት፡፡

ሐውልቶች

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በቁጥራቸው በርስት ያሉ ሓውልቶች በተለያዩ ዋና ዋና አደባባዮቿ ተተክለው ይገኛሉ፡፡ እነዚህም የአዲስ አበባ ኡነታዊ ታሪክና እንዲሁም የታሪክ ማስታወሻና ማረጋገጫ ናቸው፡፡ ከነዚህም ሃውልቶች መሃከል የተወሰኑት በተለያዩ ጊዜያት ሲፈጠሩ በነበሩት የፓለቲካ ችግር ምክንያት የወደሙ ሲሆን የተቀሩትን ግን እስከ አሁን ድረስ በተተከሉበት ቦታ ይገኛሉ፡፡

አቡነ ጴጥሮስ ሓውልት

አቡነ ጴጥሮስ በሁለተኛ ጣልያን ወረራ ጊዜ አገር ወዳድ ከሚባሉት የኢትዮጵያ ጀግኖች አንዱ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ለፀረ ቀኝ ግዛት በመንቀሳቀሳቸው በአስቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፡፡

Abune Petros Statue


የነፃነት ሐውልት

የነፃነት ሐውልት አራት ኪሎ አደባባይ ያለው ሐውልት ሲሆን ይህንም የተሰራው ጣልያን ኢትዮጵያ ለአምስት ዓመታት (1937-41) ይዟት በነበረ ወቅት ሒወታቸው ለገበሩ ጀግኖት ኢትዮጵያውያን መታሰብያ ነው፡፡

the liberation monument


የሰማዕታት መታሰቢያ ሐውልት

የስድስት ኪሎ የሰማዕታት መታሰብያ ሓውልት የተሰራው በጣልያን ቀኝ ገዢ ሃይሎች በየካቲት 12/1937 ዓ/ም ለተጨፈጨፈ 30,000 የሚያህሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መታሰቢያ እንዲሆን ተብሎ ነው፡፡

the martyrs' monument


አንድነት ሐውልት

የአንድነት መታሰቢ ሐውልት የተሰራው የኢትዮጵያ ሱማልያ በወረረችበት ወቅት የኢትዮጵያ ድምበር ለማስከበር ሂወታቸው ለሰው ጀግኖች የኢትዮጵያ ወታደሮች መታሰብያ እንዲሆን ተብሎ ነው፡፡

the Andinet statue


የዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ሐውልት

የዳግማዊ አፄ ምኒሊክ የፈረስ ሐውልት በአራዳው ጊዮርጊስ አደባባይ ይገኛል፡፡ ይህንን ሐውልት ተሰራው በልጃቸው ንግስት ዘውዲቱ ግዛት ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ሓውልቱ ሁለት ነገሮችን ያመላክታል እነሱም ፀረ ቀኝ ግዛት ትግል እና የስልጣኔ ራእይ ናቸው፡፡ ሐውልቱ ከመደብ የተሰራ ሲሆን ሃርትል ስፒንግለር የተባለ ጀርመናዊ አርኪቴክት የተቀረፀ ነው፡፡ ንጉስ የሚያጋልቡት ፈረስ አባ ዳኘው ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ፊቱ የሚመለከተው ወደ ስሜት ጦርነት የተካሄደባት ቦታ አድዋ፡፡

የአድዋ ጦርነት በመጨረሻው 19 ክ/ዘመን በወራሪው የጣሊያን መንግስትና በዳግማዊ አፄ ምኒሊክ የሚመራው የኢትዮጵያ ጦር መሃከል የተካሄደ ጦርነት ሲሆን በኢትዮጵያ አሸናፊነትም በድል ተጠናቅቀዋል፡፡

the statue of Emperor Menelik


የቀዳማዊ ዩህዳ አምበሳ ሐውልት

ቀዳማዊ የዩህዳ አንበሳ ሐውልት የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር ሃዲድ ተሰርቶ ካለቀ በኋላ 1922 ዓ.ም ተሰራ፡፡ ይህ ሐውልት አሉ ከሚባሉ አዲስ አበባ ከተማን ልዮ ከሚያደርጓት ምልክቶች አንዱ ሲሆን የብዙ ቱሪስቶች ቀልብ የሚስብ ታሪካዊ ሐውልት ነው፡፡
ጣሊያን ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረባቸው አምስት ዓመታት ጊዜ ሐውልቱ በቀኝ ገዥዎች ሃይል ከኢትዮጵያ ወደ ሮም ተወሰደ ለ60 ዓመታት ከቆየ በኋላ በተደረገው የረዥም ጊዜ የዲፕሎማቲክ ድርድር ወደ ሃገር ቤቱ ተመለሰ፡፡   

the Lion of Judah


የዳግማዊ ዮህዳ አምበሳ ሐውልት

ዳግማዊ የዮህዳ አንበሳ ሐውልት ቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ አንበሳ ተብሎም ይታወቃል፡፡ ሐውልቱ የተለየና ዘመናዊ የሆነ ስነ-ጥበብ የሚያንፀባርቅ ድንቅ ስራ ነው፡፡ ሐውልቱ ለሚመለከቱት ሰዎች በጥልቀትና በትኩረት ተመልክተው የሐውልቱ መልዕክት እንዲረዱና አድናቆታቸውን እንዲገልፁም ይጋብዛቸዋል፡፡ ሐውልቱ የተሰራው አፄ ኃይለስላሴ 25ኛ ዓመት የንግስና በዓልን ለማክበር ምክንያት በማድረግ ነው፡፡ 

the Lion of Judah II


ሴባስቶፓል የመታሰቢያ ሐውልት

ዳግማዊ የዮህዳ አንበሳ ሐውልት ቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ አንበሳ ተብሎም ይታወቃል፡፡ ሐውልቱ የተለየና ዘመናዊ የሆነ ስነ-ጥበብ የሚያንፀባርቅ ድንቅ ስራ ነው፡፡ ሐውልቱ ለሚመለከቱት ሰዎች በጥልቀትና በትኩረት ተመልክተው የሐውልቱ መልዕክት እንዲረዱና አድናቆታቸውን እንዲገልፁም ይጋብዛቸዋል፡፡ ሐውልቱ የተሰራው አፄ ኃይለስላሴ 25ኛ ዓመት የንግስና በዓልን ለማክበር ምክንያት በማድረግ ነው፡፡ 

Sebastopol


ገጾች: 1  2  3