የህዝብ ፓርኮች የህዝብ ፓርኮች

ሸገር መናፈሻ  
Sheger Gardenመናፈሻው ለሰርግ የሚያገለግሉ 15 ደሴቶች ያሉት ሲሆን የመናፈሻ ና የመዝናኛ አገልግሎት ይሰጥበታል፡፡ ሸገር መናፈሻ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8  ሰሜን መዘጋጃ አካባቢ ይገኛል፡፡ የቴኒስ፤የፑል /ከረንቡላ/ እና የህፃናት መዝናኛ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ በተጨማሪም ለተለያዩ ግብዣዎች የሚዉሉ ዕቃዎች ይከራዩበታል፡፡

ሐምሌ 19 መናፈሻ
Hamle 19 Gardenከ1933ዓ.ም ጀምሮ በመናፈሻነት እያገለገለ ያለ ሲሆን በተለያዩ ማራኪና እድሜ ጠገብ እፅዋት የተሸፈነ ነው፡፡ 33 የሰርግ ደሴቶች የዓሣ ገንዳ እና ችግኝ ጣቢያ ይገኙበታል፡፡ መናፈሻው ሶስት የፎቶ ግራፍ ቦታዎች አሉት፡፡ የእቴጌ መነን ቪላ ያለበት በመሆኑ ልዩ ድምቀት ይሰጠዋል፡፡ መናፈሻው ለመጎብኘት በግለሰብ አንድ ብር ነው፡፡

 

 

አፍንጮ በር መናፈሻ
Afencho-Ber Gardenፓርኩ ሀገር  በቀል እና ሀገር በቀል ባልሆኑ እፀዋቶች የተሸፈነ ነው፡፡ ለመናፈሻ፡ለሰርግ፡ለልደትና ፎቶ ግራፍ አገልግሎት ይውላል፡፡ በጉለሌ ክ/ከተማ ቀበሌ 06 ከአ/አበባ ዩኑቨርስቲ ወደ ጊዮርጊስ በሚወስደው መንገድ በስተ ቀኝ በኩል ይገኛል፡

ገጾች: 1  2