ዕይታ ዕይታ

በኢፌዲሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 49 ቁጥር 1 መሠረት አዲስ አበባ የፌደራል መንግስቱ ርዕስ ከተማ ናት፡፡
በዚሁ አንቀጽ ቁጥር 2 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሙሉ ሥልጣን እንዳለው የሚደነግግ ሲሆን ዝርዝር ህጉም በህግ እንደሚወሰን ባስቀመጠው መሠረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚተዳደርበትን የራሱ ቻርተር አዋጅ ቁጥር 89/87 አውጥቷል፡፡

 • በኢፌዲሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 50 ቁጥር 2 መሠረት የፌዴራሉ መንግስትና ክልሎች ሥልጣን
  • ህግ-አውጪ /Legislative Body/
  • ህግ አስፈጻሚ / Executive Body/
  • ህግ ተርጓሚ (የዳኝነት) Judiciary Body አካላት የተከፋፈለ ነው፡፡
    
 • ከላይ በተጠቀሰው የህገ-መንግስት አንቀጽ መሠረት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማዋ ትልቁ የሥልጣን ህግ አውጪ አካል ነው፡፡

  የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በከተማው በተሰጠው የሥልጣን ክልል ውስጥ ከተማ አቀፍ ህጎችን ያወጣል፣የወጡ ህጎች በአግባቡ መተግበራቸውንና ተፈፃሚነታቸውን እየተከታተለ፣ የከተማዋ ማስተር ፕላን በየ10 (አስር) ዓመቱ ሲከለስ የሚያጸድቅ፣የከተማዋን አስፈጻሚ አካላት በጀት የሚያጸድቅ፣ በየሴክተሩ የተመደቡ ዓመታዊ በጀቶች ለታለመላቸው ዓላማ መዋላቸውን የሚከታተል የከተማው ህዝብ የሉዓላዊነት መገለጫና ከፍተኛው የሥልጣን አካል ነው፡፡

የከተማው ም/ቤት በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ አዋጅ የማውጣት ሥልጣን አለው፡-

 • የከተማውን አስፈፃሚ አካላት ያቋቁማል፤
 • የከተማውን አስተዳደር በጀት ያፀድቃል፤
 • የከተማውን መሪ ፕላን ያወጣል፤
 • በከተማ ም/ቤቱ ቻርተር መሠረት የከተማውን የዳኝነት አካላት ያቋቁማል፤እንደየአግባቡ ሥልጣንና ተግባራቸውን ይወስናል፡፡
 • የከተማ አስተዳደሩን በጀት ከ65 በመቶ በላይ ለካፒታል ፕሮጀክት እንዲውሉ ታሳቢ በማድረግ ያጸድቃል፡፡
 • የከተማዋን የዳኝነት አካላት ያቋቁማል፣እንደየአግባቡ ስልጣንና ተግባራቸውን ይወስናል፡፡
 • በአዲስ አበባ አስተዳደር የወጡ ነባር ህጎችን ይተካል ያሻሽላል፡፡
 • በየሩብ ዓመቱ የከተማዋን ከንቲባ ሪፖርት ያዳምጣል፡፡

ገጾች: 1  2  3