ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ

Nefas Silk-Lafto Subcity on Mapየንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 68.3 ኪሎ ሜትር ካሬ የቆዳ ስዳት አለው፡፡ የህዝቡም ብዛት 335 ሺህ 470 ሲሆን ከዚሁ ውስጥ 158 ሺህ 126 ወንድ 177 ሺህ 614 ሴቶች ናቸው፡፡ በአንድ ኪሎ ሜትር ካሬ የሰፈሩ ሰዎች ብዛት 4915 ይደርሳል፡፡ በጽህፈት ቤቱ 2013 ወንድ፣ 2080 ሴት ቋሚ ሠራተኞች እንዲሁም 166 ወንድ 210 ሴት ኮንትራት ሠራተኞች አሉት፡፡

የትምህርት ተቋማትን በተመለከተ በክፍለ ከተማው ስድስት የመንግስት፣ 170 የግል፣ ሰባት የሕዝብ ዐጸደ ህጻናት አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን በተጨማሪም 15 የመን ግስት 104 የግል፣11 የህዝብ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ፡፡ በተያያዘም አምስት የመንግስት፣ ስምንት የግል፣ አምስት የህዝብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ሁለት የመንግስት፣ 14 የግል፣ አንድ የህዝብ መሰናዶ ትምህርት ቤቶችም ክፍለ ከተማው ውስጥ ስራቸውን በማከናወን ላይ ናቸው፡፡ ከሙያና ቴክኒክ ጋር በተያያዘ ሦስት የመንግስት እና 16 የግል ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ስድስት የግል ኮሌጆች ይገኛሉ::

ከጤና ተቋማት ጋር በተያያዘ በክፍለ ከተማው ስድስት የመንግስት የጤና ጣቢያዎች፣ 14 የግልና 19 የተቋም መለስተኛ ክሊኒኮች፣ 38 የግል መካከለኛ ክሊኒኮች እንዲሁም 18 የግል ከፍተኛ ክሊኒኮች ይገኛሉ፡፡