ልደታ ክፍለ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ

Lideta Subcity on Mapየክፍለ ከተማው የቆዳ ስፉት፡- 9.18 ካሬ/ሜ

የክፍለ ከተማው የህዝብ ብዛት፡- 214 ሺህ 769 ሲሆን ከዚህ ውሰጥ

 • የወንድ ብዛት 102 ሺህ 513፣
 • የሴት 112 ሺህ 283 ነው፡፡

በካሬ/ሜ የሠፈረ ሠው፡- ………

የክፍለ ከተማው ጽ/ቤት መገኛ ቦታ፡- አምስተኛ አካባቢ

የክፍለ ከተማው ስልጣንና ተግባር
 • ክፍለ ከተማው ባልተማከለ የሥልጣን ክፍፍል መርህ በተሠጠው የቦታ ክልል ማዘጋጃ ቤት በመሆንና ከከተማው ማዕከል ጋር በመቀናጀት ይሠራል፡፡
 • በሥሩ የሚገኙትን ወረዳዎች ያስተዳድራል
 • በአካባቢያዊ ህግና ሥርዓት የማስከር ኃላፊነት አለበት
 • የክፍለ ከተማው ምክር ቤት የሥራ ዘመን አምስት ዓመት ነው፡፡
የክፍለ ከተማው ምክር ቤት

ተጠሪነቱ ለክፍለ ከተማው ነዋሪና ለከተማው ምክር ቤት ሆኖ

 • ሀ. የክፍለ ከተማውን የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ ልማት እና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ዕቅድ ያፀድቃል
 • ለ. የምክር ቤት አፈጉባኤ፣ ምክትል አፈጉባኤ እና ፀሐፊ ከአባላቱ መካከል ይመርጣል፡፡
 • ሐ. የክፍለ ከተማውን ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አብላጫ የምክር ቤት መቀመጫ ባለው የፖለቲካ ድርጅት አቅራቢነት ከአባላቱ መካከል የመረጣል፡፡
 • መ. በክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቅራቢነት የክ/ከተማውን ቋሚ ኮሚቴ አባላትን ሹመት ያፀድቃል፡፡
 • ሠ. ከከተማው ምክር ቤት የሚመደብለትን በጀት ይደለድላል፡፡
 • ረ. የክፍለ ከተማውን ምክር ቤት ኮሚቴዎች ያቋቁማል፡፡
 • ሰ. ከክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ዓመታዊና ወቅታዊ ሪፖርት ይቀበላል፣ መርምሮ ውሳኔ ይሠጣል፡፡
 • ሸ. የክፍለ ከተማው ምክር ቤት ስለ አሠራሩ የሚወሰን ውስጠ ደንብ ያወጣል፡፡

ክፍለ ከተማው በስሩ አስር ወረዳዎች አቅፏል፡፡

በክፍለ ከተማው የሚገኙ አንጋፉ ኮሌጆችና ት/ቤቶች

ህንፃ ኮሌጅ፣ ተግባረ ዕድ ት/ቤት፣ የንግድ ት/ቤት

በክፍለ ከተማው ውስጥ የሚገኙ ተጠቃሽ ተቋማት

የከፍተኛው ፍርድ ቤት፣ የጦር ኃይሎች ሆስፒታል

በክፍለ ከተማው የተደረገ ተጠቃሽ የመልሶ ማልማት እንቅስቃሴ

በሠንጋተራና ልደታ ፍ/ቤት አካባቢ የሚገኘውን 26 ሄክታር መሬት በማፍረስ ሞዴል ሊሆኑ የሚችሉ ግንባታዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

በክፍለ ከተማው የሚገኝ ተጠቃሽ ሆቴል

ዋቢ ሸበሌ ሆቴል

የክፍለ ከተማው ካርታ