ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ

Kolfe-Keranio Subcity on Mapየኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ከሦስት ቁጥር ማዞሪያ ከፍ ብሎ ይገኛል፡፡ ክፍለ ከተማው 6125 ኪሎ ሜትር ካሬ የቆዳ ስፋት ሲኖረው የሕዝብ ብዛቱ ደግሞ 456 ሺህ 219 ነው፡፡ በኪሎ ሜትር ካሬ የሰፈረው ሰው ብዛት 7448.5 ነው፡፡

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ 4,543 ቋሚና 411 ለተወሰነ ጊዜ የቁርጥ ክፍያ (contract) ሰራተኛ በድምሩ 4954 ሠራተኞች አሉት፡፡ ክፍለ ከተማው በ2ዐዐ3 በጀት ዓመት ብር 385,537,235.ዐዐ ተበጅቶለት 5ዐ,46ዐ,325.38 ብር የካፒታል በጀት ወጪ አድርጓል:: 7,44ዐ የሥራ እድልም ተፈጥሯል፡፡

የክፍለ ከተማው ሶስት የመንግሥት፣137 የግል እና 23 መንግሥታዊ ያልሆኑ አፀደ ህፃናት ትምህርት ቤቶች አሉት፡፡ እንዲሁም 18 የመንግስት፣ 72 የግልና 22 መንግሥታዊ ያልሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ፡፡ 38 የመንግሥት፣ አስር የግል እና ስድስት መንግሥታዊ ያልሆኑ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ይዟል:: ክፍለ ከተማው የቴክኒክና ሙያ ተቋም፣ ኮሌጆች  እና ዩኒቨርስቲ  የሉበትም::

ክፍለ ከተማው 28 የግል መለስተኛ፣ 11 የግል ከፍተኛ እና 48 የግል መካከለኛ ክሊኒኮች ይዟል፡፡ አምስት የመንግሥት ጤና ጣቢያዎችን፣ ሁለት የመንግሥት ሆስፒታሎችን እና ሁለት የግል ሆስፒታሎችን ይዟል፡፡ እንዲሁም አምስት ኤምባሲዎች፣ 99 ሆቴሎች፣ 2ዐ የኦርቶዶክስ፣ 55 የእስልምና፣ አምስት የካቶሊክ እና 44 የፕሮስታንት ተቋማት ይገኙበታል፡፡