ጉለሌ ክፍለ ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማ

Gullele Subcity on Mapየጉለሌ ክፍለ ከተማ 30.18 ኪሎ ሜትር ካሬ የቆዳ ስፋት አለው፡፡ የክፍለ ከተማው የህዝብ ብዛት 284ሺህ 865 ነው፡፡ በኪሎ ሜትር ካሬ የሰፈረው ሰው 9ሺህ 438.9 ነው፡፡ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ጽህፈት ቤት በቀድሞው ውሃና ፍሳሽ መስሪያ ቤት ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ፊት ለፊት ይገኛል፡፡ የስልክ ቁጥሩ 011 - 155 19 62 ነው፡፡ ክፍለ ከተማው 3‚514 ቋሚ እና 175 ጊዜያዊ ሠራተኞች አሉት፡፡ በበጀት ዓመቱ 258 ሚሊዮን 483 ሺህ 609 መደበኛ በጀት የተመደበለት ሲሆን የካፒታል ወጪው ደግሞ 59 ሚሊዮን 956 ሺህ 445 ነው:: አስተዳደሩ በበጀት አመቱ ለ12ሺህ 764 ሰዎች የስራ እድል ፈጥሯል፡፡

ክፍለ ከተማው 58 የአፀደ ህፃናት፣ 38 የመጀመሪያ ደረጃ፣ ስምንት ሁለተኛ ደረጃ እና አምስት የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤቶች ይገኙበታል፡፡ አምስት ኮሌጆች፣ አምስት ዩኒቨርስቲዎች እና ሁለት መሰናዶ ትምህርት ቤቶች ይገኙበታል፡፡

ክፍለ ከተማው ሶስት ሆስፒታሎች፣ አንድ ከፍተኛ ክሊኒክ፣ 23 መለስተኛ ክሊኒኮች፣ ሰባት ጤና ጣቢያዎች እና አምስት ክሊኒኮች አሉበት፡፡ እንዲሁም 13 የኦርቶዶክስ፣ 12 የእስልምና፣ 12 የፕሮቴስታንት እና አስር የካቶሊክ ሃይማኖቶች ተቋማት ይገኙበታል::