ባህልና ቱሪዝም ባህልና ቱሪዝም

ራዕይ

ባህላዊ ተፈጥሮአዊና ታሪካዊ ሀብቶቹን የሚያለማ፣ የሚንከባከብና የሚጎበኝ ኀብረተሰብ በመፍጠር በ2ዐ2ዐ ዓ/ም አዲስ አበባን በዓለም ተመራጭ ከሆኑ የአፍሪካ 5 ዋና ዋና የቱሪስት መዳረሻና፣ የባህል ማዕከል ከተሞች መካከል አንዷ ማድረግ፡፡

ተልዕኮ

የከተማዋን ባህላዊ፣ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ሀብቶች የሚወድ፣ የሚጠብቅ፣ የሚያበለፅግና ወደ ልማት ኃይልነት የሚቀይር የተለወጠ ትውልድ በመፍጠር፣ ባህልና ኪነ-ጥበብን ዋነኛ የልማት ሀይል በማድረግ እና የቱሪስት መስህቦችን በማስተዋወቅ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው፡፡ ይህንንም ለማሳካት ግንዛቤ ማስጨበጥ፣ በማስተዋወቅ፣ አስተባብሮ በማሳተፍ፣ የመሪነት ሚና ይጫወታል፡፡

ዋና ዋና ተግባራት
 1. ቴአትር፣ የባህልና ዘመናዊ ሙዚቃ ማቅረብ፣ ፊልሞችን ማሳየት
 2. አገራዊ የፊልም ማዕከል በማቋቋም ፊልሞችን መስራት ዶክመንተሪ ፊልም መስራት፣ የሬዲዮ ፕሮግራሞችን ማሰራት
 3. የብሔር ብሔረሰቦች እሴቶችን ጠብቆ ማቆየትና ማስተዋወቅ
 4. የሙያ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መስጠትና የሙያ ምዝገባ ማካሄድ፣ የፊልምና የቴአትር ማሳያ ፈቃድ መስጠት/ ለውጭና ለውስጥ/
 5. በከተማ ወስጥ በኪነ-ጥበብ ዘርፍ ስልጠና የሚሰጡ ተቋማት መቆጣጠርና ፈቃድ መስጠት
 6. የኪነ-ጥበብ መረጃዎችን በተሟላና በሳይንሳዊ መንገድ ስብሰባ ማደራጀት፣ ማሰራጨት፣ ከተማ አቀፍ የኪነ-ጥበብ ፌስቲቫሎች ማዘጋጀት
 7. ከአለማቀፍና ከክልሎች ጋር ኪነ-ጥበብ አኳያ ግንኙነት መፍጠር
 8. የህዝብ ቤተ-መፃህፍት የሚቋቋሙበትንና ሚስፋፉበትን
 9. ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን፣ አሉታዊ ተጽእኖ ያላቸውን መጤ ባህሎችንና የለውጥ እንቅፋት የሆኑ አመለካከቶችን በመዋጋት የአመለካከትና የአሠራር ለውጥ ማምጣት
 10. ቅርሶችን ማጥናት መመዝገብ፣ መጠበቅ፣ እንዲመዘገቡ ማድረግ ለቅርሶች ክትትልና ጥበቃ እንክብካቤ ማድረግ፣
 11. ሙዚየሞችን ማደራጀት መምራትና አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረግ
 12. የከተማውን እምቅ የቱሪዝም ሀብት በሀገርና በአለም አቀፍ ደረጃ ጥራቱን በጠበቀና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማስተዋወቅና ገበያ መፍጠር
 13. ዘመናዊ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የቱሪስት መረጃ ማዕከል መፍጠር