ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

ስለ ቢሮው

ራዕይ

 • በ2012 ዓ.ም የተሟላ መረጃ ያለው፣ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብን ያጎለበተና በከተማው ልማት በባለቤትነት የሚሳተፍ ህብረተሰብ በመፍጠር ጠንካራ የኮሙኒኬሽን ሥርዓት ከመሠረቱ 5 የአፍሪካ ከተሞች ተርታ መሰለፍ፡፡

ተልዕኮ

 • ዘመናዊ፣ ግልፅና ፈጣን ምላሽ መስጠት ባህሉ ያደረገ የኮሙኒኬሽን ሥርዓት በመዘጋትና በዘርፉ መሪ ሚና በመጫወት በመንግስትና በህዝቡ መካከል ጥራት ያለውና ለሁሉም ነዋሪ ተደራሽ የሆነ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ማድረግ፡-
  • በዋናዋና ሃገራዊና ከተማ አቀፍ አጀንዳዎች ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር
  • የህዝቡን ትክክለኛ የመረጃ ፍላጎት ማርካት፣ ተሳትፎና ተጠቃሚነቱን በቀጣይነት ማሳደግ፤
  • የከተማውንና የሃገራችንን መልካም ገጽታ መገንባት፤

 እሴቶች

 • ተጠያቂነት
 • ግልፅነት
 • የላቀ አገልግሎት መስጠት
 • ለለውጥ ዝግጁነት
 • በእውቀትና በእምነት መመራት/መስራት፣
 • ለከተማችን ገፅታ ግንባታ ስኬት ግንባር ቀደም ሚና መጫወት፣
 • የጋራ መግባባት ለመፍጠር መትጋት፣
 • ለጊዜ ላቅ ያለ ዋጋ መስጠት፣

የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ስልጣንና ተግባር

 የከተማ አስተዳደሩ የሚያከናውናቸውን የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ተግባራት በጠንካራ የኮሙኒኬሽን ስራ በመስኩና በየደረጃው በመደገፍ ህዝቡ ተገቢውን ወቅታዊ መረጃ በሚፈለገው ጥራትና ፍትነት እንዲያገኝ ለማድረግ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በአዋጅ ቁጥር 35/2004 ዓ.ም የተሰጡት ስልጣንና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፡፡

 1. ለከተማው አስተዳደር የመረጃና የመረጃ ልውውጥ/ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን/ ስራ አመራር ይሰጣል፣ በመስኩም በየደረጃው የተሳለጠ አፈፃፀም የሚኖርበትን ሥርዓት ይዘረጋል፣
 2. ለከተማው አስተዳደር መስሪያ ቤቶችና ከከተማ እስከ ቀበሌ ባሉት የአስተዳደሩ መንግስታዊ እርከኖች ሊኖር የሚገባውን የመረጃና የመረጃ ልውውጥ አደረጃጀት ይወስናል፣ ተግባራዊ እንዲሆን ያስፈፅማል፣ ይመራል፣ ያስተባብራል፣
 3. በከተማው አስተዳደር በየደረጃው ለሚከናወነው የመንግስት መረጃ ስርአትና ልውውጥ ሥራ አቅጣጫ በመስጠት ያስተባብራል፣
 4. ለከተማው አስተዳደር የሴክተርና ሌሎች መስሪያ ቤቶች የመረጃና የመረጃ ልውውጥ ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ተግባሮችን ያከናውናል፣ ሀላፊዎቻቸውን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር በየደረጃው ባሉ የሚመለከታቸው አካላት እንዲሾሙ ያደርጋል፣ ያሰማራል፣
 5. የከተማው አስተዳደር ቃል አቀባይ ሆኖ ይሰራል፣ በየደረጃው ያለው የመረጃና የመረጃ ልውውጥ መዋቅር ወይም የመንግስት ኮሙኒኬሽን አካል ለየተመደበበት መንግስታዊ አደረጃጀት በቃል አቀባይነት ሀላፊነቱን የሚወጣበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣
 6. የከተማው አስተዳደር ዋነኛ የመረጃ ወይም የኢንፎርሜሽን ምንጭ ሆኖ ያገለግላል፣ የከተማውን አስተዳደር መልእክቶች በመቅረፅ በልዩ ልዩ መንገዶች ያሰራጫል፣
 7. በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ የከተማውን አስተዳደር አቋም ይገልፃል፣ ያስተዋውቃል፣
 8. የከተማውን አስተዳደር የመረጃ ስርጭትና ልውውጥ ፕሮግራሞች ይዘትና አፈፃፀም ያቀናጃል፣ ያስተባብራል፣
 9. የሀገር ውስጥና የውጪ መገናኛ ብዙሃን የከተማውን አስተዳደር በሚመለከት በሚያወጧቸው ዘገባዎች ላይ የቅኝት ስራዎችን ያከናውናል፣ ይተነትናል፣ ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርስ በማድረግ ምላሽ እንዲሰጥባቸው አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ህዝቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ያደርጋል፣
 10. በመንግስት ፖሊሲዎችና በተለያዩ የአስተዳደሩ ዕቅዶች፣ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች እንዲሁም በልዩ ልዩ የከተማው እና አገራዊ ጉዳዮች ላይ በህብረተሰቡ ውስጥ ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያስችል የህዝብ የውይይት መድረኮችን፣ ሁነቶችን፣ ኤግዚቢሽኖችን፣ ባዛሮችንና የጎዳና ላይ ትእይንቶችን ያዘጋጃል፣ በሴክተሮችና በክፍለ ከተሞች የሚዘጋጁ ሁነቶችን ያቀናጃል፣ ያስተባብራል፣
 11. ከፍተኛ የከተማው አስተዳደር ባለስልጣናት ህብረተሰቡን በአካል አግኝተው ማነጋገር፣ ማወያየትና ለጥያቄዎቻቸው ምላሽ መስጠት የሚችሉባቸውን የውይይት መድረኮች፣ የመስክ ጉብኝትና ጋዜጣዊ መግለጫ ያዘጋጃል፣ ያስተባብራል፣
 12. የከተማውን አስተዳደር የድረ ገፅ ስራ ይሰራል፣ በከተማው ልዩ ልዩ ደረጃዎች የመረጃ ማእከላት እንዲቋቋሙ፣ ማእከላቱ በመረጃ መረብ እንዲቀናጁ ያደርጋል፣
 13. ልዩ ልዩ የህትመት ስራዎችን ያከናውናል፣ የድምፅና የምስል ቀረፃ በማካሄድ ቅንብሮችንና ፕሮግራሞችን እንዲሁም ዶክመንተሪዎችን ያዘጋጃል፣
 14. ፎቶዎችን ያትማል፣ በአዳራሽን፣ በመስኮት ኤግዚቢሽን ለህዝብ እይታ ያቀርባል፣
 15. ለአገር ውስጥና መረጃ ለሚፈልጉ የውጭ ጋዜጠኞች በየወቅቱ መንግስታዊ መረጃ ያሰራጫል፣ መግለጫ ይሰጣል፣
 16. በከተማው አስተዳደር ውስጥ የሚሰሩትንና የሚንቀሳቀሱትን የመረጃ አካላትና ባለሙያዎች አቅም ለመገንባት የሚያስችሉትን ስልቶች ይዘረጋል፣ ተግባር ላይ ያውላል፣ ስልጠና ይሰጣል፣
 17. ስርጭታቸው በከተማው አስተዳደር ውስጥ ለሚከናወን የግል ሚዲያና የፕሬስ ባለቤቶች እንዲሁም የማስታወቂያ አገልግሎትና የህዝብ ግንኙነት ስራ ላይ መሰማራት ለሚፈልጉ ግለሰቦችና ድርጅቶች የእውቅና ፈቃድ ይሰጣል፣
 18. በከተማው አስተዳደር ውስጥ የሚዲያ መሰረተ ልማት የሚጠናከርበትን፣ የሚስፋፋበትን፣ በተገቢው ቴክኖሎጂና ብቃት ባለው የሰለጠነ ባለሙያ የሚደራጅበትን ስርአት ይቀይሳል፣
 19. በከተማው አስተዳደር የመረጃ ስርጭትና የመረጃ ልውውጥ ዙሪያ ጥናትና ምርምር ያካሂዳል፣ የህዝብ አስተያየት ቅኝትና ጥናት ያከናውናል፣
 20. በሥራው ልዩ ባህሪ ምክንያት የተለየ ሙያ ያለው የሰው ሀይል በልዩ ሁኔታ መቅጠር አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ቅጥሩን ለካቢኔው በማቅረብ ያስወስናል፣ ሲፈቀድም ያስፈፅማል፣