አራዳ ክፍለ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ

Arada Sub City

የአራዳ ክፍለ ከተማ 9.91 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ስፋት ያለው ሲሆን 225,999 ህዝብ ይኖርበታል፡፡  በኪሎ ሜትር ካሬ የሰፈረው ሰው 228ዐ5.1 ነው፡፡ በ2003 በጀት አመት 327 ሚሊዮን 444 ሺህ 176 ብር በጀት ተመድቦለታል::  

በክፍለ ከተማው በርካታ ትላልቅ ሆቴሎች፣ የህዝብ መናፈሻዎች፣ የመንግስት መሥሪያ ቤቶች፣ ፍርድ ቤቶችና የኃይማኖት ተቋማት ይገኙበታል፡፡ የክፍለ ከተማው አስተዳደር 3213 ቋሚና 227 ለተወሰነ ጊዜ የቁርጥ ክፍያ (Contract) ሠራተኞች ሲኖሩት ለ3001 ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡

የክፍለ ከተማው አስተዳደር ጽህፈት ቤት በወረዳ 9 ከምኒልክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፊትለፊት ባለው ህንፃ ላይ ይገኛል፡፡ የስልክ ቁጥሩ 0111-570171 ሲሆን  የፖስታ ሣጥን ቁጥሩ ደግሞ 25227 ነው፡፡