አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ

Akaki Kality Subcity on Mapየክፍለ ከተማው የቆዳ ስፋት፡- 118.08 ኪ.ሜ/ ካሬ

የክፍለ ከተማው የህዝብ ብዛት፡- 195 ሺህ 273 ሲሆን ከዚህ ውስጥ የወንድ ብዛት 95 ሺህ 558፣ የሴት 99 ሺህ 715
በካሬ/ሜ. የሰፈረ ሰው፡- 1653.7
የክፍለ ከተማው ጽ/ቤት መገኛ ቦታ፡- ከሲአርዲኤ መ/ቤት ቀጥሎ

የክፍለ ከተማው ሥልጣንና ተግባር

 • ክፍለ ከተማው ባልተማከለ የሥልጣን ክፍፍል መርህ በተሰጠው የቦታ ክልል ማዘጋጃ ቤት በመሆንና ከከተማው ማዕከል ጋር በመቀናጀት ይሰራል፡፡
 • በስሩ የሚገኙትን ወረዳዎች ያስተዳድራል
 • በአካባቢያው ህግና ሥርዓት የማስከበር ኃላፊት አለበት
 • የክፍለ ከተማው ምክር ቤት የሥራ ዘመን አምስት ዓመት ነው፡፡

 

የክፍለ ከተማው ምክር ቤት

 • የክፍለ ከተማውን የኢካኖሚ፣ የማህበራዊ ልማት እና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ዕቅድ ያፀድቃል
 • የምክር ቤት አፈ ጉባኤ፣ ምክትል አፈ ጉባኤ እና ፀሐፊ ከአባላቱ መካከል ይመርጣል፡፡
 • የክፍለ ከተማውን ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አብላጫ የምክር ቤት መቀመጫ ባለው የፖለቲካ ድርጅት አቅራቢነት ከአባላቱ መካከል ይመርጣል፡፡
 • በክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቅራቢነት የክፍለ ከተማውን ቋሚ ኮሚቴ አባላትን ሹመት ያፀድቃል፡፡
 • ከከተማው ምክር ቤት የሚመደብለትን በጀት ይደለድላል
 • የክፍለ ከተማውን ምክር ቤት ኮሚቴዎች ያቋቁማል፡፡
 • ከክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዓመታዊና ወቅታዊ ሪፖርት ይቀበላል፣ መርምሮ ውሳኔ ይሠጣል፡፡
 • የክፍለ ከተማው ምክር ቤት ስለ አሠራሩ የሚወስን ውሰጠ ደንብ ያወጣል፡፡

 

ክፍለ ከተማው በሥሩ 11 ወረዳዎችን አቅፏል

በክፍለ ከተማው ውስጥ የሚኙ ፋብሪካዎችና የኢንዱስትሪ ተቋማት

 • የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ቴክኖሎጂ ተቋም
 • ቴርሞ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ
 • ናይል የቡና ኤክስፐርት
 • ፋሽኮ የፕላስቲክና ጫማ ፋብሪካ
 • ገላን የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ
 • አዲስ ጐማ
 • አደዋ ዱቄት ፋብሪካ
 • አቃቂ ጋርመንት ፋብሪካ
 • አቃቂ ጨርቃጨርቅ
 • አልፉበክ አልሙኒየምና ብረት ምርቶች