ውሃና ፍሳሽ አገልገሎት ባለስልጣን ውሃና ፍሳሽ አገልገሎት ባለስልጣን

ስለ ቢሮው

የተቋቋመበት አዋጅ/ደንብ

 • በአዋጅ ቁጥር 68/1963 የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ባለስልጣን በሚል    ስያሜ
 • በአዋጅ ቁጥር 10/87 - የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ እንደገና ተቋቋመ.

የተቋቋመበት ዘመን

 • 1963 ዓ.ም.

ራዕይ

 • በ2012 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ከተማን የንፁህ ውሃ አቅቦትና የዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ደረጃ በአፍሪካ ካሉት ቀዳሚ አምስት ከተሞች ተርታ ማሰለፍ፡፡

ተልዕኮ

 • የውሃ መገኛዎችን በመጠቀም እና የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓትን በመዘርጋት፤ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራት  ከአዲስ አበባ ከተማ ፈጣን ዕድገት ጋር የሚመጣጠን የንፁህ ውሃ አቅርቦት እና የዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ለከተማዋ ነዋሪ በበቂና አስተማማኝ ሁኔታ መስጠት፡፡

እሴቶች

 • ንፁህ ውሃ ለሁሉም የከተማዋ ነዋሪ እናቀርባለን!
 • ከፍሳሽ ቆሻሻ የፀዳ ከተማ እንፈጥራለን!
 • በማያቋርጥ ለውጥ እና መሻሻል እናምናለን!
 • በዕውቀትና በእምነት እንመራለን!
 • ፈጣን ምላሽ መስጠት የዕለት ተዕለት ተግባራችን ነው!
 • ግልፅነትና ተጠያቂነት የአገልግሎታችን መገለጫዎች ናቸው!
 • ቅንጅታዊ አሰራር ለተልዕኮአችን መሠረት ነው!