አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መስመሪያ ቤት አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መስመሪያ ቤት

 

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መስመሪያ ቤት

የተቋቋበት አዋጅ፡-

በአዋጅ ቁጥር 8/1986 የኦዲትና ቁጥጥር መስሪያ ቤት በሚል የተቋቋመ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማቋቋሚያ ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/95 እና በአዋጅ ቁጥር 29/2004 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መስመሪያ ቤት በመባል ተቋቁሟል፡፡

 

የተቋቋመበት ዘመን፡- በ1986 ዓ.ም ተቋቋመ፡፡

ራዕይ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙ በሁሉም ተቋማት የላቀና ተደራሽ ኦዲት በማከናወን ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲሰፍን በመከታተልና በመደገፍ በ2012 ዓ.ም የአስተዳደሩ ሃብት ከብክነት፣ ከጥፋትና ከምዝበራ እንዲጠበቅ ማድረግ፡፡

ተልዕኮ

 • አስተዳደሩ የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ ለማገዝና የአስተዳደሩ ውስን ሃብት ለታለመለት ልማት መዋል እንዲችል፡-
 • የኦዲት ሙያ የሚጠይቀውን ደረጃ በመጠቀም በከተማ አስተዳደሩ ሥር የሚገኙ ተቋማትን ኦዲት ማድረግ፣
 • አሰተማማን መረጃ፣ ምክር እና ድጋፍ መሰጠትና
 • በግል የኦዲትና የሂሳብ ሙያ ላይ ለመሰማራት ለሚደልጉ ባለሙያዎች የሙያ ምስክር ወረቀት መስጠትና መከታተል ናቸው፡፡

እሴቶች፡-

 • ተጠያቂነት
 • ግልጽነት
 • የላቀ አገልግሎት መስጠት
 • ለለውጥ ዝግጁነት
 • በእውቀትና በእምነት መመራት/መስራት
 • የሙያ ነጻነት
 • ገንቢ አስተያየት መስጠት
 • ለሃብት ውጤታማነት መትጋት

የመ/ቤቱ ኃላፊ ስም፡-

ስም - ወ/ሮ አባይነሽ ገ/መድህን

ስ.ቁ - 251-11550 50 61