የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል

የተቋቋመበት አዋጅ

ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 18/2002፡፡

የተቋቋመበት ዘመን

ጥቅምት 30/2002 ዓ.ም

ራዕይ

በ2020 ዓ.ም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የኢትዮጵያን የዕፅዋት ዝርያዎች ምንጭነትን የሚያመለክት በዕፅዋት ዝርያዎች ምርመራና ክብካቤ እንዲሁም በትምህርትና ኢኮቱሪዝም መስህብነቱ ተምሳሌታዊ የዕፅዋት ማዕከል ሆኖ ማየት፡፡

ተልዕኮ

በአዲስ አበባ በስተሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ በጉለሌና ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተሞች በተፈቀደለት 705 ሄክታር መሬት ላይ የዕፅዋት ዝርያዎች ጥበቃ፣ የአካባቢ ትምህርት እና የምርምር ሥራዎችን በማከናወን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጎብኚዎች የኢኮኑሪዝም አገልግሎት መስጠትና ቀጣይነቱን ማረጋገጥ፡፡

እሴቶች

 •     ተፈጥሮን መንከባከብና ማድነቅ
 •     ለዕፅዋት ክብካቤና ምርምር ቅድሚያ መስጠት
 •     ዕፅዋት ህይወት መሆናቸውን ማመን
 •     የኢኮቱሪዝም ልማት
 •     ህብረተሰብ ተኮር ልማት
 •     ተጠያቂነት
 •     ተነሳሽነት
 •     በቡድን ስራ ማመን
 •     ለለውጥ ዝግጁነት
 •     ግልፅነት
 •     በእውቀትና በሃቀኝነት መስራት

የመስሪያ ቤቱ ዋና ኃላፊ

ስም - አቶ ተክሌ ወልደ ገሪማ

ስ.ቁ - 0111275332

ኢሜይል - gulbotgar@gmail.com