የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮብል ስቶን ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ.ቤት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮብል ስቶን ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ.ቤት

የተቋቋመበት ደንብ፡-

በደንብ ቁጥር 24/2002 ተቋቋመ፡፡

የተቋቋመበት ዘመን፡- ህዳር 1/2002 ዓ.ም ተቋቋመ

ራዕይ፡-

የአካባቢውን እምቅ ሀብት ጥቅም ላይ በማዋልና ጠንካራ ኢንተርፕራይዞችን በመፍጠር ድህነትና ሥራ አጥነት ተቀርፎ አዲስ አበባን በኮብስቶን ያማረችና ውብ ማድረግ፡፡

ተልዕኮ፡-

  • ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ለአንቀሳቃሾች በተለይም ወጣቶችና ሴቶች በጥርብ ድንጋይ ንጣፍ ሥልጠና በመስጠት በቂ እውቀትና ክህሎት ማስጨበጥ፣
  • ሁሉንም ባለድርሻ አካላት አቀናጅቶ በማንቀሳቀስ አሳታፊና ዘላቂ የኮብልስቶን ልማትን ማረጋገጥ፣
  • የኮብልስቶን ቴክኖሎጂን በማሸጋገር ጠንካራ ኢንተርፕራይዞችን መፍጠርና በተገኘው እውቀትና ክህሎት ደረጃቸውን የጠበቁ መንገዶች እንዲገነቡ ማድረግ፡፡

እሴቶች፡-

  • ፍትሐዊነት
  • ቁርጠኝነት
  • ተጠያቂነት
  • ግልጽነት
  • ለለውጥ ዝግጁነት
  • የላቀ አገልግሎት መስጠት
  • በእውቀትና በእምነት መምት እና መስራት፡፡

የመስሪያ ቤቱ ዋና ሃላፊ

ስም - አቶ አማረ ሺበሺ

ስልክ - 0111-57-62-33