ስፖርት ኮሚሽን ስፖርት ኮሚሽን

የተቋቋመበት አዋጅ፡-

  • የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/2003 ዓ.ም ተቋቋመ፡፡

የተቋቋመበት ዘመን፡-

  • በህዳር 3 ቀን 2003 ዓ.ም በአዋጅ ራሱን ችሎ የወጣ ሲሆን ከዚህ በፊት ከወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የተቀናጀ ነበር፡፡

ራዕይ፡-

  • በ2012 ዓ.ም ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ጤናማ ዜጋ፣ ብቃት ያለው ስፖርተኛና ተጠቃሚ የሆነ ህብረተሠብ መፍጠር፡፡

ተልዕኮ፡-

  • በከተማችን ጠንካራ ህዝባዊ መሠረት ያላቸው የስፖርት አደረጃጀቶችን በማጎልበት፣ የማዘውተሪያ ሥፍራዎችና ተቋማትን በማስፋፋት፣ የነዋሪዎቿን የስፖርት ተሣትፎ በማረጋገጥ፣ በአካልና በአእምሮ የዳበረ፣ ጤናማና አምራች ዜጋን በማፍራት በሀገር ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁመና ተወዳዳሪ የሆነ ምርጥ ስፖርተኛ ማፍራት ነው፡፡

እሴቶች

  • ተጠያቂነት
  • ግልፅነት
  • የላቀ አገልግሎት መስጠት
  • ለለውጥ ዝግጁነት
  • እውቀትና በእምነት መምራት /መስራት
  • ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ህብረተሰብና ብቃት ያለው ስፖርተኛ ማፍራት