ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ

ስለ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ

የተቋቋመበት አዋጅ፡-

 • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላትን እንደገና ለማቋቋም በወጣ አዋጅ ቁጥር 15/2001 አንቀፅ 18 መሠረት ስልጣንና ተግባራቱ ተዘርዝሮ እንደገና ተቋቁሟል፡፡

የተቋቋመበት ዘመን፡-

 • 2001 ዓ.ም ከላይ በተጠቀሰው አዋጅ መሠረት ራሱን ችሎ የወጣ ሲሆን ከዚህ በፊት በሁለት ጽ/ቤቶች ማለትም ማህበራዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጉዳይ ጽ/ቤትና የአሰራርና ሠራተኛ ጽ/ቤት በሚል አደረጃጀት ይመራ ነበር፡፡ ከዛም በፊት በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ራዕይ፡-

 • 2012 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማን የሥራ ስምሪት አገልግሎት የተስፋፋበት የኢንዱስትሪ ሠላም የሰፈነበት እና የህብረተሰቡ ማህበራዊ ደህንነት የተረጋገጠበት ከተማ ማድረግ፡፡

ተልዕኮ፡-
ቢሮው በከተማ ደረጃ ጥናትና ምርምር በማካሄድ ፖሊሲዎችን ፣ህጎችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን በስፋት በማስተዋወቅና በማስፈፀም ህብረተሰቡን በማሳተፍና  ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት ድጋፍ በመቀናጀት፡-

 • የሥራ ሥምርት አገልግሎት በማስፋፋት የሠራተኞችንና አሠሪዎችን መብት በማስጠንቀቅ እንዲሁም የሥራ አካባቢዎች እንዲሻሻሉ በማድረግና የሠራተኞችን ጤንነትና ደህንነት በማስጠበቅ እንዱስትሪ ሰላም ማስጠበቅ፣
 • የማህበራዊ ልማት ደህንነትና ልማት ፕሮግራሞችን በማስፋፋት ማህበራዊ ችግሮች ከመከሠታቸው በፊት መከላከልና በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማቋቋም ማህበራዊ ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ማድረግ ናቸው፡፡

እሴቶች፡-

 • ለለውጥ ዝግጁነት
 • ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት
 • ግልፅነት
 • በእውቀት መስራት /መምራት
 • ተጠያቂነት
 • የላቀ አገልግሎት መስጠት
 • የኢንዱስትሪ ሰላም ማስፈን
 • ተጎጂዎችን በዘላቂነት ማቋቋም
 • እሴቶች፡-
 • ለለውጥ ዝግጁነት
 • ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት
 • ግልፅነት
 • በእውቀት መስራት /መምራት
 • ተጠያቂነት
 • የላቀ አገልግሎት መስጠት
 • የኢንዱስትሪ ሰላም ማስፈን
 • ተጎጂዎችን በዘላቂነት ማቋቋም