ጤና ቢሮ ጤና ቢሮ

ስለ ጤና ቢሮ

የተቋቋመበት አዋጅ፡-

 • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈጻሚ እና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላትና እንደገና ለማቋቋም በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 25/2001 በአንቀጽ4/1 ሥር በተራ ቁጥር 7 ላይ የጤና ጥበቃ ቢሮተብሎ በአዲስ ተቋቁሟል፡፡

የተቋቋመበት ዘመን፡-

 • በጥር ወር 1985 ዓ.ም በኢትዮጲያ የሽግግር መንግስት ጤና ጥበቃ ሚኒስተር የአዲስ አበባ  አስተዳደር አካባቢ ጤና መምሪያ በሚል ስያሜ ስልጣንና ተግባር ተሰጥቶት ሕጋዊ ሰዉነት አግኝቶ እንዲሰራ ከተደረገ በኋላ በዛዉ ዓ.ም በየካቲት ወር በክልል 14 አስተዳደር ጤና ቢሮ  በሚል ስያሜ ለመጀመሪያ ጊዜ በቢሮ ደረጃ ተቋቋመ፡፡

ራዕይ፡-

 • በ2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ከተማ ጤናዉን በራሱ የሚያመርት ማህበረሰብ ያላትና ጥራት ያለዉ የጤና አገልግሎት የሚሰጥባት የአፍሪካ ሞዴል ከተማ ማድረግ፡፡

ተልእኮ፡-

 • የአዲስ አበባ ከተማ ህብረተሰብንና ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ የበሽታ መከላከል ስራ በመስራት  ቀልጣፋ ዉጤታማና ጥራት ያለዉ የጤና አገልግሎት  በመስጠት ጤናማና አምራች ዜጋ መፍጠር፡፡

እሴቶች፡-

 • ተጠያቂነት
 • ግልጽነት
 • የላቀ አገልግሎት  መስጠት
 • ለለዉጥ ዝግጁነት
 • በእዉቀትና በእምነት መምራት/መስራት
 • ለሙያ ስነምግባር ተገዥነት
 • ህሙማንን መርዳት ተቀዳሚ ተግባራችን ነዉ፡፡