ታህሳስ 4/2011 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰላም ልዑካንን ወደ ተለያዩ ክልሎች ልታሰማራ ነው

 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን 150 የሰላም ልዑካንን ወደ ተለያዩ ክልሎች ልታሰማራ መሆኑን አስታወቀች፡፡

የመንበረ ፓትሪያሪክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አባ ዲዮስቆርዮስ በሰጡት መግለጫ ስምሪቱ ከታህሳስ 10 ቀን 2011 ዓመተ ምህረት ይጀምራል ብለዋል።

የሰላም ልዑኩ በሰላም ማስፈን ስራው ከመሰማራቱ በፊትም ሰላምን ለማስፈን የሚያስችሉ አስተምህሮት እንደሚሰጥም ዋና ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉ የሰላም እጦቶችን ለማስቀረትና ሰላምን ለማስፈን ቤተክርስትያኗ ኃላፊነት እንዳለባትም ነው የተገለጸው፡፡

ይህንንም ለማሳካት ከቤተክርሲቲያኒቱ የተውጣጡ የሃይማኖት አባቶች የሰላም ልዑክ ቡድን በቅዱስ ሲኖዶስ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት መቋቋሙ ተነግሯል፡፡

ህብረተሰቡ ሃይማኖታዊ እሴቱን በመጠቀም ሀገርን ከሚጎዱ ተግባራት እንዲቆጠብ፥ ከመንግስት እና ከባለ ድርሻ አካት ጋር በመሆን ማስተማር እንደሚያስፈልግ አባ ዲዮስቆርዮስ ተናግረዋል፡፡

              ምንጭ:-  ኤፍ.ቢ.ሲ


ዜናዎች እና ለውጦች ዜናዎች እና ለውጦች