ህዳር 22/20011 ዓ.ም ወጣቶች ከስሜታዊነት ወጥተዉ ምክንያታዊ በመሆን በቀሰሙት ትምህርት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር ራስን በእዉቀት ማነጽ ቀዳሚ ትኩረት ሊያደርጉ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

ዘንድሮ በመድናችን አዲስ አበባ ለ13ኛ ጊዜ የሚከበረዉን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን አከባበርን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ ተማሪዎች ፌስቲቫል ተካሂዷል፡፡
የዕለቱ የክብር እንግዳ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ እንደተናገሩት በአዲ አበባ ከተማ አስተዳደርና ህዝብ አስተናጋጅነት የሚከበረዉ ይህ በዓል የሚኖረዉ ፋይዳ ለከተማዉ ብቻ ሳይሆን ለሀገራችን ጭምር በመሆኑ ለከተማዋና ለሀገራችን የገፅታ ግንባታ የላቀ አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡ ይሁንና ትምህርት የእኩልነት፣ የልማትና የሰላም ግባችን እዉን ለማድግ ወሳኝ መሣሪያ በመሆኑ የወጣቱን የትምህርት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማጎልበትና የስነዜጋና ስነ ምግባር ትምህርትን በማጠናከር አዲሱን ትዉልድ ዲሞክራሲያዊ አስተሳስብ ያለዉ ዜጋ አድርጎ በመቅረጽ ረገድ የመምህራንና የወላጆች ድርሻ ቀላል አይደለም ፡፡ ወጣቶች ከስሜታዊነት ወጥተዉ ምክንያታዊ በመሆን በቀሰሙት ትምህርት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር ራስን በእዉቀት ማነጽ ቀዳሚ ትኩረት ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡ 
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ በበኩላቸዉ የዘንድሮዉን የ13ኛዉን የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል ለየት የሚያደርገዉ በአስተሳሰብ ቀረፃና አመለካከት ለዉጥ ላይ አተኩሮ በመሥራት አለመግባባቶች እና ቅሬታዎች በእርቅና በመቻቻል እንዲፈቱ በማድረግ አንድነትን እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር ዓላማ ያደረገ በመሆኑ ነዉ ብለዋል፡፡
የዘንድሮዉ 13ኛዉ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል “በብዝሃነት የደመቀ የኢትዮጵያዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ይታወቃል፡፡


ዜናዎች እና ለውጦች ዜናዎች እና ለውጦች