ህዳር 19/2011 የአዲስ አበባ ወጣቶች ሐዋሳ ገቡ

የአዲስ አበባ ወጣቶች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ሐዋሳ ገቡ፡፡

በዛሬው ዕለት ወደ ሐዋሳ ያቀኑት 300 የሚሆኑ የመዲናዋ ወጣቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ወጣቶቹ ሐዋሳ ሲደርሱ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ  ዶክተር ጌታሁን ጋረደው እና የከተማዋ ነዋሪዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በሁለት ቀናት የሃዋሳ ቆይታው የህዝብ ለህዝብ ውይይትን ጨምሮ በመዲናዋ ወጣቶች ዘንድ የተጀመረው የበጎ ፈቃድ ባህል በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች እንዲስፋፋ ለማስቻል ይወያያል ተብሏል፡፡

እንዲሁም ጉዞው በአዲስ አበባ እና በሀዋሳ ከተሞች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የሚደረግ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሰል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶች በቀጣይነትም የሚያካሂድ መሆኑን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

                       ምንጭ፡-ኤፍ.ቢ.ሲ


ዜናዎች እና ለውጦች ዜናዎች እና ለውጦች