Back

ታህሳስ 18/ 2011 የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት እና የውጭ ዲፕሎማት በተገኙበት ዛሬ በይፋ ተመርቋል።

ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ የጉለሌ የፅፅዋት ማዕከል ለከተማዋ ህዝብ ተጨማሪ ሃብት መሆኑን ገልፀው በከተማዋ ዳርቻ ላይ ያለውን አረንጓዴ ፀጋ ወደ መኃል ከተማ ለማምጣት የከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ 
ለሚቀጥሉት 6 ወራት የዕፅዋት ማዕከሉ ጎብኚዎችን የሚያስከፍለውንም ክፍያ የከተማ አስተዳደሩ እንደሚሸፍን ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል።
በአጠቃላይ 705 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የዕፅዋት ማዕከሉ ለበርካታ የከተማችን ወጣቶች የስራ እድል እንደሚፈጥር ገልፀዋል፡፡


ዜናዎች እና ለውጦች ዜናዎች እና ለውጦች