ታህሳስ 17/2011 በመሶብ ቅርፅ ዲዛይን የተደረገ ባለ 70 ወለል ህንፃ በአዲስ አበባ ለማስገንባት ማሰቡን የባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር ይፋ አድርጓል፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር በማህበራዊ ድረገፁ ላይ ባወጣው መረጃ በኢትዮጵያውያን አርክቴክቶች ዲዛይኑ የተሰራውን ህንፃ እውን ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማድረግ መጀመሩን አስታውቋል፡፡
ህንፃው የመሶብ ቅርፅ የያዘበት ምክንያትን ከኢትዮጵያውያን ቤት የማይጠፋው መሶብ ተምሳሌትነቱ የመሰባሰብ፣ የአንድነት፣ የደስታና የጋራ ቃልኪዳን የሚታሰርበት በመሆኑ ነው ተብሏል፡፡
ህንፃው ሲገነባ የሆቴልና ቱሪዝም ስራ ማሰልጠኛ ተቋምን የልህቀት ማእከል ከማድረጉም በላይ የአገራችንን ገጽታ በመገንባት የቱሪስት መዳረሻ ሊሆን እንደሚችልም ዲዛይኑን የሰሩት ባለሞያዎች አስታውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያውያንን አኗኗር ያሳያል የተባለው ህንፃ 250 ሜትር ከፍታ ያለው ባለ 70 ወለል ህንፃ ነው፡፡
ህንፃው በውስጡ የተለያዩ ደረጃቸውን የጠበቁ ባህላዊና ዘመናዊ ሆቴሎች፣ የገበያ ማዕከል፣ ሁሉንም ክልሎች የሚወክል የባህል ማእከል፣ የጎልፍ ሜዳ፣ የልዩ ልዩ ስፖርት ማዘውተሪያ፣ ቢሮዎች እና የቱሪዝምና ሆቴል ዘርፍ የልህቀት ማእከል እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡
ህንፃው እውን ሲሆን በርዝመቱ ከአፍሪካ የመጀመሪያው ይሆናል፡፡
EBC


ዜናዎች እና ለውጦች ዜናዎች እና ለውጦች