ህዳር 17/2011 ኢትዮጵያና ብሪታንያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

 ኢትዮጵያና ብሪታንያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር መስማማታቸው ተገለፀ።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር ሃሪያት ባልዲውን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል ።

በቆይታቸውም ኢትዮጵያና ብሪታንያ የሚኖራቸውን የኢንቨስትመንትና ንግድ ግንኙነት እንዲሁም ሌሎች ትብብሮችን ለማጠናከር የሚያስችል ስምምነት አድርገዋል።

በውይይቱም በአሁኑ ወቅት በሁለቱ ሀገራት መካካል ያለው የንግድ ልውውጥ ከ2 ቢሊየን ዶላር በላይ መድረሱ ነው የተገለፀው።

ብሪታንያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና መረጋጋት ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ ትስስሩ የበለጠ እንዲጎለበት ያላሰለሰ ጥረት  እንድምታደርግ ምክትል ሚኒስትሯ ሃሪያት ባልዲውን መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

                   ምንጭ፡-ኤፍ.ቢ.ሲ


ዜናዎች እና ለውጦች ዜናዎች እና ለውጦች