ታህሳስ 19/ 2011 የአዲስ አበባ የኔትወርክ ጥራት ችግር በ3 ወራት ውስጥ ይፈታል፡- ኢትዮ-ቴሌኮም
በአዲስ አበባና ዙሪያዋ የሚታየውን የኔትወርክ ጥራት መጓደል በሶስት ወራት ውስጥ መፍታት የሚያስችል የኔትወርክ ማስፋፊያ ስራ እያከናወነ መሆኑን ኢትዮ-ቴሌኮም አስታወቀ፡፡
መርካቶን ጨምሮ ቦሌ አራብሳ፣ ኃይሌ ጋርመንት፣ ጀሞና፣ ቦሌ አካባቢዎችና በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ ቦታዎች የሞባይል ኔትወርክና የኢንተርኔት አገልግሎት ጥራት መጓደል በስፋት ይስተዋላል፡፡
በእነዚህ ቦታዎች ያለውን የኔትወርክ ጥራት መጓደል በአጭር ጊዜ ለመፍታት ኢትዮ-ቴሌኮም ፕሮጀክት ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ በመስሪያ ቤቱ የኔትወርክ ዲቪዥን ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ ኃይለመስቀል በተለይ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡
የኔትወርክ ችግሩም የተከሰተው በዋናነት በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱና በቦታው ያለው ኔትወርክ በመጨናነቁ ነው ብለዋል፡፡
በእነዚህ ቦታዎች ያለውን የኔትወርክ አቅም ለመጨመር የሚስችሉ ዕቃዎች ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ በዚህ ሳምንት መግባታቸውንምአቶ ቴዎድሮስ ገልፀዋል ፡፡
በመዲናዋ በተመረጡ ቦታዎች ጥቅም ላይ የሚውሉት ዕቃዎቹ የኔትወርክ ጥራት ችግሩን ከመፍታት ባለፈ ተጨማሪ 500 ሺህ ደንበኞችን የማስተናገድ አቅም አላቸው ብለዋል፡፡
የኔትወርክ ማስፋፊያው ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ በሁለት ወር ከግማሽ ጊዜ ውስጥ ችግሩ እንደሚፈታ ተመልክቷል፡፡
ይህ የመፍትሄ ውጥን በፊትም አሁንም ኔትወርክ በሌለባቸው ቦታዎች መፍትሄ የሚሰጥ ሳይሆን የኔትወርክ ጥራት መጓደል በሚታይባቸው ቦታዎች ማሻሻያዎችን ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል፡፡
በዘላቂነት የሞባይል ኔትወርክና የኢንተርኔት አገልግሎት የመቆራረጥ ችግርን ለመፍታት የኔትወርክ አቅምን ከመጨመር ባለፈ አማራጭ የኤሌክትሪክ ሀይልን ለመጠቀም እተየሰራ እንደሆነም ኢትዮ-ቴሌኮም አስታውቋል፡፡
EBC
NEWS Archive
-
ታህሳስ 19/ 2011 የአዲስ አበባ የኔትወርክ ጥራት ችግር በ3 ወራት ውስጥ ይፈታል፡- ኢትዮ-ቴሌኮም
-
ታህሳስ 18/ 2011 የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት እና የውጭ ዲፕሎማት በተገኙበት ዛሬ በይፋ ተመርቋል።
-
ታህሳስ 18/2011 አቶ አበበ አበባየሁ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ
-
ታህሳስ 17/2011 በአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ላይ ያተኮረ ጉባዔ እየተካሄደ ነው
-
ታህሳስ 17/2011 በመሶብ ቅርፅ ዲዛይን የተደረገ ባለ 70 ወለል ህንፃ በአዲስ አበባ ለማስገንባት ማሰቡን የባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር ይፋ አድርጓል፡፡
-
ታህሳስ 17/2011 የ2018 የአፍሪካ ታሪክ ሰሪዎች በቢቢሲ
-
ታህሳስ 16/2011 የትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ጠዋት ላይ በላምበረት መናሃሪያ ድንገት ጉብኝት አደረጉ
-
ታህሳስ 16/2011 የዕደ ጥበብ አምራቾች ምርታቸውን ለህዝብ እና ለደንበኞቻቸው በመጭው በዓላት እንደሚያቀርቡ የአዲስ አበባ ከተማ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡
-
ታህሳስ 15/2011 አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን አስመረቀ
-
ታህሳስ 14/2011 ጠቅላይ ሚነስትር ዶክተር ዓብይ አሕመድ የሪፐብሊኩ የጥበቃ ሃይል አባላት ጋር ተገናኙ
-
ታህሳስ 14/2011 ባለፉት 5 ወራት 800 ሰዎች የምህረት አዋጁ ተጠቃሚ ሆኑ
-
ታህሳስ 14/2011 የከተማችን ሴቶች በሚካሄደዉ ማንኛዉም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እድገት ከፍ ያለዉን ድርሻቸዉን ሊወጡ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡
-
ታህሳስ 13/2011 የባህል እሴትና እና የባህል ኢንዱስትሪ ልማትን በማረጋገጥ የከተማችንን ሁለንተናዊ እድገት አናፋጥናለን! (የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ)
-
ታህሳስ 13/2011 የሚኒስትሮች ም/ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከተወያየ በኋላ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡
-
ታህሳስ 13/2011 ለረጅም ጊዜ ሳይለማ የቆየ እና ባለቤትነቱ የመንግስት ልማት ድርጅቶች የሆነ 10.2 ሔክታር መሬት ወደ መሬት ባንክ ገቢ ሆነ፡፡