ኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ ኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ

About the Bureau

የተቋቋመበት አዋጅ፡- አዋጅ ቁጥር 15/2000
የተቋቋመበት ዘመን፡- ግንቦት 2000ዓ.ም
ራዕይ፡-

አዲስ አበባ ከተማን በ2012 ዓ.ም መካከለኛ ገቢ ካላቸው ከተሞች ጋር ተወዳዳሪ የሆኑ ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶችና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት የተሟሉላት ማግረግ፡፡

ተልዕኮ፡-

የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪቿን ፍላጉት መሠረት በማድረግ፡-

 • በመንግሥትና በህዝብ ተሳትፎ የሚገነቡ የቤትና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ዲዛይኖችና ግንባታዎች በጥራት እንዲከናወኑና ከድህነት ቅነሳ ስትራቴጂ ጋር እንዲቀናጁ ማደረግ፡፡
 • በመንግሥትና በህዝብ የተሰሩ ግንባታዎችን የአስተዳደሩ ቤቶች በአግባቡ እንዲተዳደሩ ማድረግ፡፡
 • በአምራቶችና በአስመጪዎች የሚቀርቡ የግንባታ ግብአቶች ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆኑ ማስቻል፡፡
 • በመንግሥት የሚገነቡ ግንባታዎች ወጪ ቆጣቢ እንዲሆኑ አማራጭ የግንባታ ግብአቶች ማምረትና ተግባር ላይ አንዲውሉ ማድረግ፡፡
እሴቶች
 • ግልደጽነት
 • ተጠያቂነት
 • የላቀ አገልግሎት መስጠት
 • በዕውቀትና በእምነት መመራት
 • ለለውጥ ዝግጁነት
 • ጥራትና ወጪ ቆጣቢነት
 • ፍትሃዊነት

ልዩ መገለጫ፡-

በከተማ አስተዳደሩ እየተገነቡ ያሉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እንዲሁም የመንግሥትና የማህበራዊ ተቋማት ግንባታ የመስሪያ ቤቱ የሥራ ውጤቶችና መገለጫዎች ናቸው፡፡