ራዕይ
- በ2012 ዓ.ም አዲስ አበባን ፍትህ የሰፈነባት እና የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ከተማ ማድረግ
ተልዕኮ
- በአዲስ አበባ ከተማ የተቀላጠፈ አገልግሎት በነፃነት፣ በገለልተኛነትና ህግን መሠረት በማድረግ ለህብረተሰቡ በመስጠት የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ማድረግ
ዕሴቶች
- ተጠያቂነት
- ግልጽነት
- ተቋማዊ ነጻነት
- ለለውጥ ዝግጁነት
- የላቀ አገለልግሎት መስጠት
- በእውቀትና በእምነት መመራትና መስራት
- ለፍትህና ለህግ የበላይነት በጽናት መታገል
- ኪራይ ሰብሳቢነትን በፅናት መታገል
የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት
የአዲስ አበባ ከተማ ፍ/ቤት በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/95 መሠረት በሁለት ደረጃ ማለትም በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እና በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ተደራጅቶ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማቋቋሚያ ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀፅ 41 እና በቻርተሩ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 408/96 ተዘርዝረው የተቀመጡ በቀጥታ የሚመጡ ጉዳዮችን እንዲሁም የቀበሌ ማህበራዊ ፍ/ቤቶች በሚሰጧቸው ውሣኔዎች ላይ የሚቀርቡ የይግባኝ አቤቱታዎችን ያያል፡፡