ቋሚ ኮሚቴዎችና  አሰራራቸው

 • የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት አስፈጻሚ አካላትን የሚከታተሉና የሚቆጣጠሩ  እንዲሁም የሚወጡ አዋጆችን ተፈፃሚነት የሚከታተሉ 6(ስድስት) ቋሚ ኮሚቴዎችን በም/ቤቱ መተዳደሪያ ደንብ ቁጥር 2/2001 መሠረት አዋቅሯል፡፡

እያንዳንዱ ቋሚ ኮሚቴ 7 (ሰባት) አባላቶች ሲኖሩዋቸው የየራሣቸው የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ ም/ሰብሳቢና ፀሐፊ አላቸው፡፡
እነሱም፡-

 • የመንግስት በጀትና ወጪ አስተዳደር ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤
 • የማህበራዊ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤
 • የማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤
 • የህግና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤
 • የሴቶች ፣ህፃናትና፣ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤
 • የከተማ ልማትና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤

በየደረጃው የሚገኙ ም/ቤቶች አደረጃጀትና የቋሚ ኮሚቴዎች ብዛት

 • የከተማዋ ነዋሪ ህዝብ የሉዓላዊነት መገለጫ የሆነው የከተማዋ ም/ቤት አወቃቀር በየደረጃው የከተማ፣የክፍለ ከተማና የወረዳ ም/ቤቶችን ያቀፈ ሲሆን እያንዳንዳቸው በሉዓላዊነት አንዱ በአንዱ ስልጣን ጣልቃ ሳይገባ የተሰጣቸውን ስልጣን ማዕከል ባደረገ መልኩ በመደጋገፍ ህዝባዊ ተልዕኮአቸውን በመወጣት ላይ ይገኛሉ፡፡

ከከተማ እስከ ወረዳ የም/ቤቶች አመራር ግንኙነትን በተመለከተ

 • በም/ቤቱ የሥራ ዘመን መጀመሪያ የከተማው ም/ቤት ከከተማ እስከ ወረዳ ም/ቤት ለሚገኙ ም/ቤቶች በም/ቤት አሠራር ኃላፊነት ዙሪያ በሁሉም ደረጃ ለጠቅላላ የም/ቤት አባላት(38 ሺህ) ስልጠና ይሰጣል፡፡
 • የዕቅድ ኦረንቴሽን በማዘጋጀት የም/ቤት አመራሮች እቅዳቸውን የጋራ ያደርጋሉ፡፡
 • የከተማው ም/ቤት ከክ/ከተማው እንዲሁም የክ/ከተማው ከወረዳው ጋር በየ 15ቀኑ የግንኙነት ጊዜ አላቸው፡፡
 • የከተማው ም/ቤት የክ/ከተማውን እንዲሁም የወረዳውን ዕቅድ አፈፃፀም ይገመግማል፡፡

በቋሚ ኮሚቴዎችና በአስፈፃሚዎች መካከል ያለ የሥራ ግንኙነት

 • የከተማው ም/ቤት በስሩ በተዋቀሩ ቋሚ ኮሚቴዎች አማካኝነት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ያሉ አስፈፃሚ አካላትን የመቆጣጠር የመከታተልና ተግባራትን ያከናውናል፡፡
 • ምክር ቤቱ የክትትል፣ቁጥጥርና ድጋፍ ተግባራትን የሚያከናውነው እያንዳንዱ ቋሚ ኮሚቴ የሚከታተሏቸውን አስፈፃሚ አካላትና ሴክተር መስሪያ ቤቶች በዝግጅት ምዕራፍ ላይ ዕቅድ ላይ በመወያየት የሚያወጧቸው ዓመታዊ ዕቅዶች፤ከከተማ አስተዳደሩ መሪ ዕቅድ፣ከ5 ዓመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እንዲሁም ከምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች (Millenium Development Goal) አንፃር የታቀደ መሆኑን በመገምገም፤አስፈላጊውን የማስተካከያ ሐሳብ ይሰጣል፡፡
 • የሴክተር መስሪያ ቤቶቹን የሩብና የግማሽ አመት ፣የ9 ወር እና የዓመቱን የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርታቸውን በማዳመጥ ፤በዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እያቀረቡት ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ለማነፃፀር በተመረጡ ሴክተሮች ላይ ከህብረተሰቡ የተገኙ አስተያየትና ጥቆማንም መሠረት በማድረግ የሱፐርቪዥን ተግራትን ያከናውናሉ፡፡
 • ከዚህ በተጨማሪም የተለያየየ መገናኛ ብዙሀን አግባቦችን በመጠቀም ከከተማው ነዋሪዎች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመመርመር በሚመለከታቸው የሴክተር መስሪያ ቤቶች ላይ የመስክ ጉብኝት በማድረግ እና ለየሴክተር መስሪያ ቤቱ ምክር ቤቱ የሚያፀድቃቸው በጀቶች ለታለመለት ዓላማ ማዋሉን በማረጋገጥ የክትትል፣ቁጥጥርና ድጋፍ ተግባራትን ያከናውናል፡፡
 • በመስክ ምልከታና በሱፐርቪዥን የተገኙ ግኝቶችን የከተማው ከንቲባ የሁሉም የሴክተር ቢሮ ኃላፊዎች ፣የክፍለ ከተማ ም/ቤት አመራሮችና የክ/ከተማ አስፈፃሚ አካላት በሚገኙበት ስለታዩ ግኝቶችና በተስተዋሉ ችግሮች ዙሪያ ውይይት በማድረግ መፍትሄ አቅጣጫ ይቀመጣል፡፡
 • በክ/ከተማና በወረዳ የሚገኙ ቋሚ ኮሚቴዎችም በተመሳሳይ በየደረጃቸው የሚገኙ አስፈፃሚ አካላትን ከላይ በከተማው ም/ቤት በተቀመጠው መሠረት ክትትል ቁጥጥርና ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡

በየደረጃው የሚገኙ ቋሚ ኮሚቴዎች የዕርስ በዕርስ ግንኙነትን በተመለከተ

 • በከተማ ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ ደረጃ የተዋቀሩት ም/ቤቶች በክፍለ ከተማ ደረጃ ደግሞ በተመሳሳይ ዘርፍ ኮሚቴ በሚል ተዋቅረዋል፡፡
 • በየወሩ የግንኙነት ጊዜ አላቸው፤እነዚህ በክፍለ ከተማ የተዋቀሩ ኮሚቴዎች በከተማ ደረጃ ለሚገኘው ኮሚቴ ዕቅዳቸውን የጋራ ካደረጉ በኋላ የወር፣የ 3 ወር፣የ 6 ወር፣የ 9 ወር እና የዓመት የዕቅድ አፈፃፀም በየደረጃው የክ/ከተማው ለከተማው ም/ቤት በተመሳሳይ የወረዳው ለክ/ከተማ ም/ቤት ያቀርባሉ፤
 • ከዚህ በተጨማሪም የከተማው ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች የአመቱን እቅዳቸውን ከክ/ከተማው ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ጋር የጋራ የማድረግ እንዲሁም የክ/ከተማ ኮሚቴዎች ከከተማው ቋሚ ኮሚቴዎች ጋር በየወሩ የግንኙነት ጊዜ ጠብቀው ይገናኛሉ፡፡

የከተማው ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ክትትልና ቁጥጥር ተግባር ሲያከናውኑ የክ/ከተማ ም/ቤት ኮሚቴዎች ሚና

 • የከተማ ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ክትትልና ቁጥጥር ሲያደርጉ የክ/ከተማ ኮሚቴዎች በተመረጡ ክ/ከተሞችና ወረዳዎች ከሚመለከታቸው ወረዳ ኮሚቴዎች ጋር በጋራ በመሆን ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋሉ፡፡

በአስፈፃሚ አካላት በደል ደርሶብኛል በሚል የሚቀርብን አቤቱታ በተመለከተ

 • የም/ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች ለሱፐርቪዥን ከመንቀሳቀሳቸው በፊት በሚዲያና በተለያዩየ መገናኛ መንገዶች በአካልም ጭምር ቅሬታና አስተያየት በማሰባሰብ ትክክለኛነቱን መሬት ወርደው የሚመለከቱበት ሁኔታ አለ፡፡
 • ከዚህ በተጨማሪም ለአፈ-ጉባኤው በተለያዩ ጊዜያት የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ በአፈጉባኤው አማካኝነት ከተመራ በኋላ በባለሙያ ትንታኔ ተሰጥቶበት ለሚመለከተው አካል ችግሩ እንዲፈታ በደብዳቤ የሚገለጽበት አሠራር አለ፡፡

አቤቱታ የሚቀርብባቸው ጉዳዮችና ጥቆማዎች

 • ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ረገጣ እና ጥሰት
 • በፍ/ቤት ሂደት ላይ ያልሆነ ወይም የመጨረሻ እልባት ያልተሰጠው ጉዳይ መሆን አለበት
 • በህዝብ ሀብትና ጥቅም ላይ የሚደርሱ ሙስናዎች
 • ሕገመንግስቱን አደጋ ላይ የሚጥሉ እና የመንግስት ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን የሚያደናቅፉ አደገኛ ተግባሮች
 • በሕዝቦች መካከል ግጭት ሊያስነሱ የሚችሉ ሁኔታዎች
 • ከፍተኛ የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ሲደርስ የሚሉ ናቸው፡፡

Pages: 1  2