መጋቢት 02 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ የከተማ ግብርናን በዘመናዊ መንገድ በማደራጀት ለነዋሪዎች ተጨማሪ የስራ ዕድል ለመፍጠር እየተሰራ ነው ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነ ታከለ ኡማ በከተማ ግብርና እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

የከተማው የወንዝ ዳርቻ ልማት አካል የሆነው የከተማ ግብርና ነዋሪው የተጎዳ አከባቢን መልሶ እንዲያገግም ከማድረግ በተጨማሪ የራስ የምግብ ፍጆታን በመሸፈን ቀሪውን ለገበያ በማቅረብ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኙ አስችሏል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የከተማ ግብርናን ለማዘመን የተሰሩ ስራዎችን ተዘዋውረው የጎበኙት / ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ በዘርፉ የተሰማሩ አካላትን ከመደገፍ ጎን ለጎን ሌሎች ተጨማሪ ወጣቶችን በማህበር በማደራጀት ገቢ እንዲያገኙ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ በዘርፉ ላይ ያሉ ችግሮችን በመቅረፍ የከተማ ግብርናን በዘመናዊ መልኩ በማደራጀት ከተማዋ የያዘችውን የአረንጓዴ ልማት ከግብ ለማድረስ እንደሚሰራ / ታከለ ኡማ ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ  የከብት እርባታን ጨምሮ በፍራፍሬ ምርት  ንብ ማነብ እንዲሁም አትክልትን በማምረት ስራ  ከሁለት ሺህ በላይ የሚሆኑ ወጣቶች እና እናቶች  ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡


NEWS Archive NEWS Archive