Back

በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችን የህይወት ታሪክ መረጃ መዝግቦ ይይዛል

የአዲስ አበባ ከተማን ውስብስብ አግሮቸን  ለመቅረፍ የከተማው  አስተዳደር በየጊዜው  የተለያዪ ስልቶችን በመንደፍ አስፈጻሚ መ/ቤቶችን  ለአገልግሎት አሠጣጥ  በሚያመች  መልኩ በማዋቀርና  በማጠናከር ዓይነተኛ  ለውጦችን  በማስመዝገብ ላይ ይገኛል፡፡  በዘስተዳደሩ የሲቪል ሰርቨስ ኤጀንሲ አዋጅ ቁጥር 6/2000 በአንቀጸ 61/1  ላይ በግልጽ  እንደተቀመጠው  የሲቪል ሰርቨስ ኤጀንሲ የመንግሥት  ሠራተኞችን መረጃ  የማደራጀት ኃላፊነት  እንዳለበትና ለዚህም ኤጀንሲው በአገር አቀፍ ደረጃ  የወጣውን  የሰው ኃብት  ሥራ  አመራር  መረጃ ሥርዓት እንዲተገበር፣ የአስተዳደሩን የመንግሥት  ሠራተኞት  የሰው ኃብት መረጃ ቋት እንደሚያደራጅና የመንግሥት ሠራተኞችን የሚመለከት  ስትስቲካዊ መረጃዎችን  እንደ ሚያሰባስብ ይደነግጋል፡፡እንደሚታወቀው መረጃ  ለመንግስት የፖሊሲ ውሳኔ፣  የስራ ፕሮግራም ለመንደፍ፣  ለበጀት አያያዝ፤ ፣ለሰውኃይል ስምሪት፣  ለዕቅድ  ዝግጅት  በአጠቃላይ ለኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖሊሲ  ጠቀስ ሠራዎች የሚያገለግል  ዋጋ የሚጨምር መሣሪያ  ነው፡፡ ይህ  መረጃ  ደግሞ በተፈበገው ጊዜና መልኩ  ዝግጁ ሊሆንይገባል፡፡